Catering and Cafeteria Services

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለተቋሙ የዕለት ተዕለትና የዓመታዊ ሥራ አፈጻጸም የሚያስፈልጉትን የሆቴልና መስተንግዶ አገልግሎቶች፣ የተሽከርካሪዎች ጥገናና ተያያዥ የጋራዥ አገልግሎቶች፣ የጉዞ ወኪል አገልግሎትና የአየር ትኬት አቅርቦት፣ እንዲሁም የህትመት አገልግሎትና የህትመት ውጤቶችን ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎችና አገልግሎት ይፈልጋል

Description

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

በአራት ሎቶች የተከፋፈለ የተለያዩ አገልግሎቶችና አቅርቦቶች ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለተቋሙ የዕለት ተዕለትና የዓመታዊ ሥራ አፈጻጸም የሚያስፈልጉትን የሆቴልና መስተንግዶ አገልግሎቶች፣ የተሽከርካሪዎች ጥገናና ተያያዥ የጋራዥ አገልግሎቶች፣ የጉዞ ወኪል አገልግሎትና የአየር ትኬት አቅርቦት፣ እንዲሁም የህትመት አገልግሎትና የህትመት ውጤቶችን ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ለአንድ ዓመት በውል ለማግኘት፣ ግዥዎቹን በአራት ሎቶች (lots) በመከፋፈል በግልጽ ጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. የግዥው ዓይነትና የሎት ክፍፍል

ሎት

ዥው ዓይነት

ዋና ዋና የአገልግሎት/አቅርቦት ይዘት

ሎት 1

የሆቴልና መስተንግዶ አገልግሎቶች

የሙሉ ቀንና የግማሽ ቀን የስብሰባ፤ የሥልጠናና የወርክሾፕ አገልግሎት፣ የስብሰባ አዳራሽና ተያያዥ መሣሪያዎች፣ የምግብና የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የእንግዳ መኝታ ክፍሎች፣ የበይነ መረብ አገልግሎትና በጨረታ ሰነዱ የተዘረዘሩ ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች

ሎት 2

የተሽከርካሪዎች ጥገናና ተያያዥ የጋራዥ አገልግሎቶች

በነዳጅና በኤሌክትሪክ ለሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች መደበኛና ወቅታዊ ሰርቪስ፣ አስቸኳይ ጥገና፣ የሞተርና የመካኒካል ክፍሎች ጥገና፣ የኤሌክትሪክና የኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ጥገና፣ የታፒሴሪ ሥራና ሌሎች ተያያዥ የ ጋራዥ አገልግሎቶች

ሎት 3

የጉዞ ወኪል አገልግሎትና የአየር ትኬት ግዥ

ለተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጉዞዎች የሚያስፈልጉ የአየር ትኬቶች፣ ተያያዥ የጉዞ ወኪልነት አገልግሎቶችና ሌሎች ተመሳሳይ የጉዞ አገልግሎቶች

ሎት 4

የህትመት አገልግሎትና የህትመት ውጤቶች ግዥ

የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣ የህትመት አገልግሎቶች፣ ተያያዥ የህትመት ቁሳቁሶችና በጨረታ ሰነዱ የሚዘረዘሩ ሌሎች ተያያዥ አቅርቦቶች

 2. ለሎቶች የመወዳደር ሁኔታ

2.1. ተጫራቾች በሕጋዊ ፈቃዳቸው፣ በሙያ ብቃታቸውና በአገልግሎት አቅማቸው መሠረት ለአንድ ሎት፣ ለብዙ ሎቶች ወይም ለሁሉም ሎቶች መወዳደር ይችላሉ።

2.2. እያንዳንዱ ሎት እንደ ተለየ የግዥ ክፍል ተቆጥሮ ለብቻው ይገመገማል፣ ውጤቱም ለብቻው ይወሰናል።

2.3. አንድ ተጫራች ለከአንድ በላይ ሎቶች ለመወዳደር ከፈለገ፣ ለእያንዳንዱ ሎት የተወሰኑትን የሕጋዊነት፣ የሙያ፣ የቴክኒክ፣ የፋይናንስና የአፈጻጸም ብቃት መስፈርቶች ማሟላት አለበት።

2.4. ተጫራች ለብዙ ሎቶች ተወዳድሮ የየሎቱን መስፈርቶች ካሟላ ከአንድ በላይ ሎት ሊያሸንፍ ይችላል።

3. የውል ጊዜና የአገልግሎት አፈጻጸም

ከየሎቱ አሸናፊ አሸናፊዎች ጋር የሚፈጸመው የአገልግሎትና/ወይም የአቅርቦት ውል ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሲሆን፣ አገልግሎቱና አቅርቦቱ በተቋሙ ተጨባጭ ፍላጎት፣ በጨረታ ሰነዱ፣ በአሸናፊው የተቀበለ ዋጋና በውሉ በሚወሰነው የአፈጻጸም ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል።

የአንድ ዓመት ውል መፈጸሙ ተቋሙ በጨረታ ሰነዱ የተመለከተውን ግምታዊ መጠን በሙሉ እንዲገዛ ወይም እንዲጠቀም ግዴታ አይፈጥርበትም፤ ትክክለኛው መጠን በተቋሙ ፍላጎትና በሚሰጠው የአገልግሎት/የአቅርቦት ትዕዛዝ መሠረት ይወሰናል።

4. የጋሪ የተሳትፎና የሕጋዊነት መስፈርቶች

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግዥ ዓይነት አግባብነት ያለውና በሥራ ላይ ያለ የታደሰ

የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ TIN፣ VAT የታክስ ክሊራንስ፣ በተመሳሳይ ሥራ ያላቸውን ልምድ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ የተገለጹ ሌሎች የሕጋዊነት፣ የብቃት፤ የቴክኒክና የፋይናንስ መስፈርቶችን ማቅረብና ማሟላት አለባቸው።

5. በየሎቱ የሚፈለጉ ልዩ የብቃትና የቴክኒክ መስፈርቶች

5.1.ሎት 1 የሆቴልና መስተንግዶ አገልግሎት

ተጫራቾች ከሚመለከተው ሥልጣን ያለው አካል የተሰጠና በሥራ ላይ ያለ የ3 ወይም 4 ኮከብ የሆቴል ደረጃ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

በተጨማሪም የሐላል ምግብ ዝግጅትና አቅርቦት መስፈርቶችን የማሟላት ብቃት፣ ተገቢ የስብሰባ አዳራሽ፣ የምግብ አገልግሎት፣ የመኝታ ክፍሎች፣ የመኪና ማቆሚያ፣ የመስገጃና የውዱእ ማድረጊያ ቦታ፣ ንጹሕ መጸዳጃ ቤቶች፣ የድምፅና የፕሮጀክተር መሣሪያዎች፣ አስተማማኝ የበይነ መረብ አገልግሎትና በጨረታ ሰነዱ የተገለጹ ሌሎች መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው፡፡ ተቋሙ የቀረቡትን መረጃዎችና የሆቴሉን አገልግሎት አቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በቦታው በመገኘት ሊያረጋግጥ ይችላል።

5.2.ሎት 2 የተሽከርካሪዎች ጥገናና የጋራዥ አገልግሎት

ተጫራቾች በቂና ተገቢ የጥገና ቦታ፣ የሥራውን ዓይነት ለመፈጸም የሚያስችሉ መሣሪያዎች፣ ብቁ የቴክኒክ ሰው ኃይልና በተመሳሳይ የተሽከርካሪ ጥገና ሥራ ያላቸውን ልምድ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው።

ተቋሙ የጋራዡን፣ የመሣሪያዎቹንና የሰው ኃይሉን ብቃት በቦታው በመገኘት ሊያረጋግጥ ይችላል።

5.3. ሎት 3 — የጉዞ ወኪል አገልግሎትና የአየር ትኬት

ተጫራቾች የአየር ትኬት ሽያጭና የጉዞ ወኪልነት አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከተው አካል የተሰጠና በሥራ ላይ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ ወይም ማረጋገጫ፣ በተመሳሳይ ሥራ ያላቸውን ልምድ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችና በጨረታ ሰነዱ የተገለጹ ሌሎች የብቃት፣ የቴክኒክና የፋይናንስ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው።

በተጫራቾች የሚቀርቡ የብቃት፣ የቴክኒክ፣ የልምድና ሌሎች ማስረጃዎች በተቋሙ ሊረጋገጡ ይችላሉ።

5.4. ሎት 4  የህትመት አገልግሎትና የህትመት ውጤቶች

ተጫራቾች ቋሚና የተሟላ የማተሚያ ቦታ፣ ለሥራው አስፈላጊ የህትመት መሣሪያዎች፣ ብቁ የቴክኒክ ሰው ኃይልና በተመሳሳይ ሥራ ያላቸውን ልምድ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የተቋሙን የቅጂ መብት ማክበር፣ በጨረታ ሰነዱ የተገለጹትን የህትመት ጥራት፣ የቴክኒክ፣ የብቃትና ሌሎች መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

ተቋሙ የቀረቡትን የማተሚያ ቦታ፣ መሣሪያዎች፣ የሰው ኃይልና ሌሎች የብቃት መረጃዎች በቦታው በመገኘት ሊያረጋግጥ ይችላል።

6. የጨረታ ሰነድ መግዣ

ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል፣ ከጳጉሜን 2 ቀን 2018 ዓ.ል. ጀምሮ እስከ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ል. ድረስ በመደበኛ የሥራ ቀናትና ሰዓታት፣ በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት፣ የግዥና ፋይናንስ ክፍል፣ ቢሮ ቁጥር B006 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

አንድ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ጊዜ በመግዛት ፈቃዱና ብቃቱ በሚፈቅደው መጠን ለአንድ፣ ለብዙ ወይም ለሁሉም ሎቶች መወዳደር ይችላል።

7. የጨረታ ማስከበሪያ

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት እንደሚከተለው የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፦

  • ሎት 1 የሆቴልና መስተንግዶ አገልግሎት፣ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤
  • ሎት 2 የተሽከርካሪ ጥገናና ተያያዥ የጋራዥ አገልግሎት፣ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤
  • ሎት 3 የጉዞ ወኪል አገልግሎትና የአየር ትኬት ግዥ፡ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤
  • ሎት 4  የህትመት አገልግሎትና የህትመት ውጤቶች ግዥ፣ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤

የጨረታ ማስከበሪያው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የተሰጠና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቋሙ በሚያቀርበው የመጀመሪያ የጽሑፍ ጥያቄ መሠረት የሚከፈል የባንክ ዋስትና መሆን አለበት።

የጨረታ ማስከበሪያው የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 (ሃያ ስምንት) ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት።

ለከአንድ በላይ ሎቶች የሚወዳደር ተጫራች ለሚወዳደርበት እያንዳንዱ ሎት ከላይ የተወሰነውን የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለበት።

8. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ሳይለወጥ ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።

9. የጨረታ ሰነዶች አቀራረብ

ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነዳቸውን አንድ “ዋና (Original) እና አንድ ቅጂ (Copy)፣

እንዲሁም የፋይናንስ ሰነዳቸውን አንድ “ዋና” (Original) እና አንድ “ቅጂ” (Copy) በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው።

የቴክኒክ ሰነዶች፣ የፋይናንስ ሰነዶችና ዋናው የጨረታ ማስከበሪያ በየራሳቸው በተለያዩ ፖስታዎች በአግባቡ ታሽገው፣ ሁሉም በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ ተደርገው መቅረብ አለባቸው።

ለብዙ ሎቶች የሚወዳደር ተጫራች የሚወዳደርባቸውን ሎቶች በግልጽ በመለየት የየሎቱን የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ በጨረታ ሰነዱ በሚወሰነው አቀራረብ ለይቶ ማቅረብ አለበት።

በዋናውና በቅጂው ሰነድ መካከል ልዩነት ካለ ዋናው (Original) ሰነድ ተቀባይነት ይኖረዋል።

በውጫዊው ፖስታ ላይ የተጫራቹ ሕጋዊ ስምና አድራሻ፤ የጨረታው ቁጥር፤

የሚወዳደርበት/ባቸው የሎት ቁጥር ቁጥሮችና የግዥው ዓይነት በግልጽ መጻፍ አለበት።

በተጨማሪም በውጫዊው ፖስታ ላይ፦ “ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት አይከፈት" የሚል ጽሑፍ በግልጽ መጻፍ አለበት።

10. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ

በትክክል የተዘጋጁና የታሸጉ የጨረታ ሰነዶች በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት፣ የግዥና ፋይናንስ ክፍል፣ ቢሮ ቁጥር B006 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከተወሰነው የመዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ መግባት አለባቸው።

11. የጨረታ መዝጊያ

ጨረታው መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ል. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡ ከተወሰነው የመዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

12. የጨረታ መክፈቻ

የጨረታው የቴክኒክ ሰነዶችና የጨረታ ማስከበሪያዎች መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ል. ጠዋት 4፡30 ሰዓት በተቋሙ የስብሰባ አዳራሽ፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታሉ።

ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።

የቴክኒክ ምዘናውን ላለፉ ተጫራቾች የፋይናንስ ሰነዶች የሚከፈቱበት ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጽሑፍ ይገለጽላቸዋል።

13. የጨረታ ምዘናና የአሸናፊ አወሳሰን

13.1 የሁሉም ሎቶች ግምገማ በቅድመ ብቃት፣ በቴክኒክና በፋይናንስ መስፈርቶች መሠረት በየሎቱ ለብቻው ይከናወናል።

13.2 ዝርዝር የምዘና መስፈርቶች፣ የቴክኒክ ማለፊያ ነጥብና የፋይናንስ ምዘና ዘዴ በጨረታ ሰነዱ ይገለጻሉ።

  • ሎት 1 የሆቴልና መስተንግዶ፡ የቅድመ ብቃትና የቴክኒክ ምዘናውን ካለፉት ተጫራቾች መካከል በፋይናንስ ምዘናው ዝቅተኛውን ተገምጋሚ ዋጋ ያቀረበውና ውሉን በብቃት ለመፈጸም የሚችለው ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
  • ሎት 2 የተሽከርካሪ ጥገናና የጋራዥ፡ የቅድመ ብቃትና የቴክኒክ ምዘናውን ካለፉት ተጫራቾች መካከል በፋይናንስ ምዘናው ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውና ውሉን በብቃት ለመፈጸም የሚችለው ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
  • ሎት 3 የጉዞ ወኪልና የአየር ትኬት፡ የቅድመ ብቃትና የቴክኒክ ምዘናውን ካለፉት ተጫራቾች መካከል በፋይናንስ ምዘናው ተወዳዳሪና ተገቢ ዋጋ ያቀረበውና ውሉን በብቃት ለመፈጸም የሚችለው ተጫራች/ተጫራቾች አሸናፊ ይሆናል/ሉ፡፡
  • ሎት 4 የህትመት፡ የቅድመ ብቃትና የቴክኒክ ምዘናውን ካለፉት ተጫራቾች መካከል በፋይናንስ ምዘናው ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውና ውሉን በብቃት ለመፈጸም የሚችለው ተጫራች/ተጫራቾች አሽናፊ ይሆናል/ሉ።

አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ያገኘው ውጤት በሌላ ሎት ላይ በራሱ ተፈጻሚ እይሆንም።

14. የማብራሪያ ጥያቀና የጨረታ ማስተካከያ

ተጫራቾች ስለጨረታው የሚፈልጉትን ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው ጊዜናአሠራር መሠረት በጽሑፍ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በጨረታው ይዘት፣ መስፈርት፣ የማቅረቢያ ሁኔታ ወይም በጨረታው ውጤት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችልማብራሪያ፣ ለውጥ ወይም ማስተካከያ ካለ፣ የጨረታ ሰነዱን ለገዙ ተጫራቾች ሁሉ በጽሑፍና በእኩል ሁኔታ ይገለጻል።

15. የጨረታ ሰነዱ ይዘት

የጨረታ ሰነዱ ቢያንስ የሚከተሉትን ይይዛል፦

  • የየሎቱ የአገልግሎትና/ወይም የአቅርቦት ዝርዝርና ወሰን፤
  • የጥራትና የቴክኒክ መስፈርቶች፤
  • የቅድመ ብቃትና የብቃት መስፈርቶች፤
  • የጨረታ ምዘና ዘዴና የቴክኒክ ማለፊያ መስፈርቶች፤
  • የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ
  • የአገልግሎት የአቅርቦት አፈጻጸም ሥርዓት፣
  • የውል ሁኔታዎች፤
  • እንዲሁም ለየሎቱ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች።

16. ጨረታውን ስለመሰረዝ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አግባብነት ባለው የግዥ ሕግ፣ ደንብ፣ መመሪያና የተቋሙ አሠራር መሠረት፣ በበቂና በሰነድ በተደገፈ ምክንያት፣ ጨረታውን በሙሉ፣ በከፊል ወይም አንድን/ከአንድ በላይ ሎት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

17. አድራሻና ተጨማሪ መረጃ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

ዋና መሥሪያ ቤት፤ የገዥና ፋይናንስ ክፍል፤ ቢሮ ቁጥር B006

ኮልፌ ቀራንዮ ከፍስ ከተማ (ጦር ኃይሎች)፣ ከሆላንድ ኤምባሲ አጠገብ

ስልክ፡ 0906 808 058 / 0911 091 766

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-17 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
  • Buyer TIN: 0002844823
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
  • Posted at: 2026-09-07T15:05:37.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders