Vehicle and Machinery Sale
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ኪራይ ተከራይ በውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የካፒታል ዕቃ ተከራይ ስም |
የሚሸጠው ንብረት |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የሐራጅ ደረጃ
|
ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
|
አቶ ሀብታሙ አበጋዝ
|
ኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን
|
64,991,747.97
|
ቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ክ/ከ በተከራዩ የማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
1ኛ
|
በተከራዩ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4፡00-6፡00 |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስVAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሽያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።
3. ድርጅቶችን በመወከል በሽያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን እና አሰፈላጊ ሰነድ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
4. የጨረታው አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።
5. የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
6. የጨረታው አሸናፊ 15 የተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
7. አሸናፊ ተጫራች ማሽኑን ካለበት ማምረቻ ቦታ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባለቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል።
8. ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-211-66-87 ላይ መደወል ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-24 12:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 20%
- Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T07:40:32.000Z
- Source: 2merkato