Chemicals and Reagents
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሶዴም ሃይፖ ክሎራይት 10%፣ ሰርፌስ ፓምፕ እና ቧንቧ መገጣጠሚያ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ፤
የጨረታ ቁጥር 01/2019
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችም፡-
1. ሶዴም ሃይፖ ክሎራይት 10%
2. ሰርፌስ ፓምፕ
3. ቧንቧ መገጣጠሚያ
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል።
1 በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
3. ለጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት / በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ የሚችሉ፣
4. ድርጅቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፓስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ከ/ውሃ/አገ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል። በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም፡፡
7. ሰርፌስ ፓምፕ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያችሁን እና ቴክኒካል ሰነዳችሁን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማስገባት ይኖርባችኋል።
8. በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደማ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ ድርጅቱ አይሸፍንም ።
10. ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል።
11. ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ።
አድራሻ፡- ደ/ማ/ከ/የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ:-0587716840፣ 0587711058፣ 0587711520
ማሳሰቢያ፡-
1. ኬሚካሉ በየወሩ ተከፋፍሎ በዓመቱ ውስጥ የሚመጣ መሆኑ ይታወቅ
2. የቧንቧና መገጣጠሚያ እቃዎች ድርጅቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በመምጣት የእቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን፤ የእቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የእቃን አይነት እንጂ የእቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መታችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን።
3. ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-23 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debre Markos City Water and Sewerage Service
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T07:57:19.000Z
- Source: 2merkato