Textile, Garments and Uniforms

በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ
  • ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት4 አላቂ የህክምና እቃዎች
  • ሎት 5 አላቂ የት/ት እቃዎች
  • ሎት 6 አላቂ የፅዳት እቃዎች
  • ሎት7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች(የኤሌክትሪክ እቃዎች
  • ሎት 8 ፕላንት ማሽነሪ ጥገና
  • ሎት 9 ፕላንት ማሽነሪ መግዥያ (ኮምፒተሮች)
  • ሎት 10 ቁሳቁስ ተገጣጣሚ መግዥያ
  • ሎት 11 ውሃና ቆሎ

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ የተመዘገባችሁ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ
  2.  የዘመኑን ግብር ከፍላችሁ ያጠናቀቃችሁ
  3. ጥቃቅንና አነስተኛ ያደራጃቸው ከሆነ ከአደራጃቸው ተቋም ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ
  5.  በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገባችሁ

 ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በእያንዳንዳቸው

  • ሎት 1. 2000/ሁለት ሺህ ብር
  • ሎት 2. 5000/አምስት ሺህ ብር
  • ሎት 3. 1200/አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር
  • ሎች 4 1000/አንድ ሺህ ብር
  • ሎት 5. 7000/ሰባት ሺህ ብር
  • ሎት 6, 4200/አራት ሺህ ሁለት መቶ ብር
  • ሎት 7, 500/አምስት መቶ ብር/
  • ሎት 8, 800/ስምንት መቶ ብር
  • ሎት 9. 2500/ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር
  • ሎት 10. 2000/ሁለት ሺህ ብር
  • ሎች 11, 500/አምስት ሺህ ብር

ዝርዝር ጨረታውን የያዘውን ሰነድ 400/ አራት/ መቶ ብር በመክፈል በት/ቤቱ የፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ ፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው ተጫራቾች ጨረታ አሸንፈው ውል ሲዋዋሉ የውል ማስከበሪያ የአጠቃላዩን ዋጋ 10 ፐርሰንት ይከፍላሉ ፡ ፡የጨረታው ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ ሲ.ፒ.ኦ ደግሞ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፡፡ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ መሙያ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተታታይ የስራ ቀናት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 02 ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ላይ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ በፋይናን የስራ ሂደት ተወዳዳሪዎች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡

ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ውድድሩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

አድራሻ ፤ ፈረንሳይ ጉራራ 12/55/64 ቁጥር ማዞሪያ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0111549331 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ::

በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02  ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-18 09:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Higher 12 Secondary School
  • Buyer address: ፈረንሳይ ለጋሲዮን ልዩ ስሙ ጉራራ 12 ቁጥር እና 55 ቁጥር አውቶቡስ ማዞሪያ ከኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን በስተጀርባ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T07:58:07.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders