Office Furniture
በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር
አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ መለያ ቁጥር GGWW/004/2019
በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት መደበኛ በጀት ለአንጮት 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ግብዓት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ለግዢ የቀረቡ እቃዎችና የጫረታ ማስከበሪያ CPO
- ሎት አንድ ፡ ፈርኒቸሮች ፈርኒቸር፡ የጫረታ ማስከበሪያ 20000ብር
- ሎት ሁለት ፥ ኤሌክትሮኒክስ ፡ የጫረታ ማስከበሪያ 20000ብር
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ፡-
1. የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት ና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦላይን /online/ ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት።
3. በጫረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጫረታ ስነዱ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 ብር/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታው ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5 ተጫራቾች የጫረታውን ቴክኒካል ና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡
ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ፣ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና
ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶከመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት ከገ/ጉ/ ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጫረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።
7. የጫረታው ሰነድ በ10ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፦
1. በግዢ ኤጀንሲ አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም
2. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው የመድሀኒት የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆኑን።
3. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው ማንኛውም እቃ የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማእከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116 ኪ.ሜ ነው።
4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
ለበለጠ መረጃ 011 336 0631 / 011 336 0148
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-17
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-17 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Gurage Zone Gedebano Gutazer Welene Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ 20000 ብር
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T08:19:55.000Z
- Source: 2merkato