House Furniture

በሸገር ከተማ አስተዳደር የቱፋ ሙና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ እቃዎች (furniture’s)፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች (stationeries)፣ የኤሌክትሮኒክሰ ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ አስተዳደር የቱፋ ሙና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴከተር መ/ቤቶች

  • ቋሚ የቢሮ እቃዎች (furniture’s) ፣
  • ቋሚ አላቂ እቃዎች፣
  • የፅዳት እቃዎች፣
  • የጽህፈት መሳሪያዎች (stationeries) ፣
  • የኤሌክትሮኒክሰ ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታአወዳድሮ መግዛት

 ስለሚፈልግ፤ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋራ ተያይዞ በቀረበው እስፔስፈኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

የጨረታ መመሪያ ፡-

  1. በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ በተጠቀሰው የስራ መስኮች የተሰማራችሁ ነጋዴዎች የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ ገዝ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ የተመዘገቡና ግብር መክፈሉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሳተፍ ትችላላችሁ።
  2. ተወዳዳሪው በፖስታ ላይ የድርጅቱን ስምና ማህተም ፣ የተወዳደሩበትን ዝርዝር ዕቃ አይነት አድራሻውን ስልክ ቁጥሩን እና ፈርማውን ማስቀመጥ የሚችል።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) በCPO ብቻ በቱፋ ሙና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው።
  4. የተወዳዳሪው ሰነድ ላይ ግልጽና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት ፤ተጫራቾች የቀረበውን እስፔሰፈኬሽን በመተው ዋጋ ሞልተው ቢገኙ ባቀረብነው እስፔሰፈኬሽን እንደተሞላ ሆኖ ይወሰዳል።
  5. የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል በቱፋ ሙና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ21ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚህው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቱፋ ሙና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሚከፈት ይሆናል፤ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም።
  8. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ ከሆኑ በኃላ በ10(አስር) ቀን ውስጥ ውል መግባት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው የጨረታው ውጤት ተገልጾ እስከ 5(አምስት) ቀን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ። ከዚህ ቀን በኃላ የመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም።
  10. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ለሁሉም እቃዎች (VAT) ጨምሮ መሙላት እና አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን የእቃ አይነቶች እስከ መስሪያ ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
  11. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ፡- ቱፋ ሙና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት / 0913432968 /0998809347 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በሸገር ከተማ አስተዳደር የቱፋ ሙና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ21ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-28 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ21ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በሸገር ከተማ አስተዳደር የቱፋ ሙና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T08:33:35.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders