Products and Services

የምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የብቸና መረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የምግብ አቅርቦት ከመደበኛ በጀት መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የብቸና መረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የምግብ አቅርቦት ከመደበኛ በጀት መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የእህል ምርት ውጤቶች ጤፍ፣ ሎት 2. የእህል ምርት ውጤቶች በቆሎ፣ ሎት 3. የእህል ምርት ውጤቶች አተር እና ጓያ እንዲሁም ጎመንዘር፣ ሎት 4. የእህል ምርት ውጤቶች በርበሬ፣ ሎት 5. የእህል ምርት ውጤቶች ቅመማ ቅመም፣ ሎት 6.የእህል ምርት ውጤቶች ፊኖ ዱቄት፣ ሎት 7. የምግብ ምርቶች ስኳር እና ዘይት እንዲሁም የዳቦ እርሾ እና ፓውደር፣ ሎት 8 የምግብ ምርቶች ጨው እና ሎት 9. አትክልት እና ፍራፍሬ ሽንኩርት እና ቃሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ መሟላት የሚገባቸው፡-

1. በዘርፉ አግባብነት ያላቸው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ   የሚችሉ፡፡

2. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ግዴታ ተመዝጋቢዎች ውጭ የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ብቻ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዝጋቢ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለሁሉም ሎቶች ከጨረታው አሸናፊ ላይ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

3. ለሁሉም ሎቶች ጨረታ ሲሞሉ ህጋዊ ማህተም እንዲሁም ፊርማ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ፓስታው ላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ለእያንዳንዱ ሎቶች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመያዝ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቸና ማረሚያ ቤት የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት 1. እስከ ሎት 9 ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ -1 ገቢ በማድረግ ኮፒውን ማያያዝ አለባቸው፡፡

6. ከሎት 1 እስከ 9 ላሉ ግዥዎች አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማቅረብ አለበት፡፡

7. ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ያሉ ሎቶች ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፓስታ በማድረግ  ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ለሁሉም ሎቶች ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ በተቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. ከሎት 1 እስከ ሎት 9 በጨረታ ሰነዶች ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆኑ ነገሮች መኖር የለበትም፡፡ ካለም ፓራፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

9. በባለሙያ የሚረጋገጡ ዕቃዎችን በባለሙያ እያረጋገጡ የምንረከብ መሆኑን እና አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ብቸ/ማረ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላጊውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

10. በእያንዳንዱ ሎት መስሪያ ቤቱ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች በየሎቱ ምድቡ 
የቀረቡትን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ /ውድቅ ይሆናሉ፡፡

11. ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሳይቀይር ከዕቃው ከጠቅላላ መጠን ላይ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ አሸናፊው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት እነ/ወ/አቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡

12. ከሎት 1 እስከ 9 የሞሉትን ዋጋ ኦርጅናሉን እና ሲፒኦ ብሎ በማሸግ በተጨማሪ ግልጽ በሆነ መልኩ የሞሉበትን ቀበሌና ጎጥ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡

13. ከሎት 1 እስከ 9 ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ30 ቀናት ይሆናል፡፡

14. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል፣ የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በማጠቃለያ ፓስታ በማሸግና በፖስታው ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

15. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ዋጋ መሙላት ሲኖርባቸው በራሳቸው ዋጋ መሙያ ከሞሉ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡

16. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 05 05 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የብቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-09-22 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bitchena Correctional Facility
  • Bid bond: 3,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎቶች
  • Published on: Be'kur (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T08:39:12.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders