Spare Parts and Car Decoration Materials

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በጠቅላላ አገልግሎት ስር ለሚገኙ ለቀላል እና የከባድ ተሽከርካሪዎች ግልጋሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር መሰፋ /ብ/ግ/ጨ/02/2019

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በጠቅላላ አገልግሎት ስር ለሚገኙ ለቀላል እና የከባድ ተሽከርካሪዎች ግልጋሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የቀላል እና የከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ /vat registration certificate/፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርተፊኬት የብቃት ሰርተፊኬት tax clearance certificate የመንግሥት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከመከላከያ ሠ/ፋ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም ብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረለት/ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሠራዊት ፋዉንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ፋይናንሺያል ሰነድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 001 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው።

5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡00 ሰዓት ላይ ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በዕለቱ ከቀን 8፡30 መ.ሰ.ፋ ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል

6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን በጽሑፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።

7.ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡-

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስዳው ላንድ ማርክ ሆስፒታል

ስልክ ቁጥር 0115572752

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-24 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Force Foundation
  • Buyer address: ከደንበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት ጫካ ቡና አጠገብ
  • Bid bond: 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T08:54:01.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders