Equipment and Accessories

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 09/2019

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ

  • የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣
  • የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን፣
  • የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣
  • የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣
  • የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾችበሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን።

በመሆኑም

1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር (ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።

3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALIY CUSTOMS BRANCH OFTCE በባንክ አሰርተዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

.

የቅ//ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

. ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት

የእቃ ግልፅ

እስከ 05/01/2019

06/01/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል።

የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አ.አቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።

8. ከላይ በተ/ቁ 8. በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. መ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011 470-85-03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

በአዲስ አበባ የቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 09:45
  • Bid opening: 2026-09-16 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Kality Customs Branch Office
  • Buyer address: ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T09:58:42.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders