Stationery
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and Accessories
Amhara
More tags
Electrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksConstruction Machinery and EquipmentTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceSpare Parts and Car Decoration MaterialsFuel and LubricantsOffice FurnitureFurniture and FurnishingAmharic2merkatoዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
Description
የአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት በ2019 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የጽህፈት መሳሪያ ፣
- የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ፣
- የግንባታ ግብዓቶች፣
- የደንብ ልብስ፤
- የፅዳት እቃዎች፣
- የቋሚ አላቂ እቃዎች፣
- የመኪና መለዋወጫ፣
- የመኪና ዘይትና ቅባት እና የመኪና ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ተጫራቾች (ድርጅቶች) መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ያላቸው።
- ጠቅላላ የሞሉት የጨረታ ዋጋ ከብር 50,000/አምስት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተ.አ.ታ ተመዝጋቢ መሆን አለበት ።
- ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌላም መረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በሁለት ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው ማቅረብ አለባቸው።
- የሁሉንም እቃዎች ዝርዝር እስፔስፊኬሸን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ ካስቀመጠው ውጭ በራሱ ጊዜ እስፔስፍኬሸን የጨመረና የቀነሰ ወይም ያስቀመጠ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30-6፡00 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግልፅ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /በሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሚወዳደሩበት ሰነዱ ላይ ከአንዱ ዋጋው እና ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ከጨረታው ከውድድሩ⁄ ውጭ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የሚለውን በጥንቃቄ ለያይተው መሙላት አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈፀሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20 % (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት።
- በማንኛውም ሁኔታ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት እንደማይኖረው መታወቅ አለበት።
- የደንብ ልብስ (የሰራ ልብስ) ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ተቋሙ በሚያቀርበው የደንብ ልብስ ናሙና መሰረት ማቅረብ እንዳለባቸው መታወቅ አለበት።
- የኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና የግንባታ ግባቶች ወደ ንብረት ከፍል ገቢ ከመደረጋቸው በፊት በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተረጋግጠው ገቢ የሚሆኑ መሆኑ መታወቅ አለበት።
- ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ /በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለፅበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት።
- መ/ቤቱ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ከኦርጅናል ሰነዱ ላይ የንግድ ፍቃዱን ኮፒ አድረጎ ፖስታው ላይ የማያስገባ ወይም ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ ሳያስገባ ውጭ ላይ የተወ ከውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን ይታወቅ።
- የጨረታ አሸናፊው አካል ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቀጥታ በአስቸኳይ በውሉ መሰረት ንብረቱን ዝ/ወ/በሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ አለበት።
- ይህ ውድድር ለ1/ አንድ/ አመት ሙሉ ስለሆነ ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች በአመቱ ውስጥ ሲያስፈልግ የሚያቀርብ መሆኑን ይታወቅ።
ለበለጠ መረጃ 0334620050/53/49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30-6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-22 14:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T10:10:22.000Z
- Source: 2merkato