Textile, Garment and Leather

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ በወረዳ 07 ስር የሚገኘው ቤተል አንደኛና መካከለኛ ት/ቤት የተለያዩ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ በወረዳ 07 ስር የሚገኘው ቤተል አንደኛና መካከለኛ ት/ቤት የተለያዩ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ማለትም፡-

  • ሎት 1 ደንብ ልብስ
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 3 የህትመት ስራ
  • ሎት 4 የህክምና ዕቃዎች
  • ሎት 5 የፅህፈት ዕቃዎች
  • ሎት 6 የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 7 ለተለያዩ መሳሪያዎችና መጽሀፍ
  • ሎት 8 የማሽነሪ ጥገናዎች
  • ሎት 9 የተገጣጣሚዎች ዕድሳትና ጥገና
  • ሎት 10 መሰረተ ልማት
  • ሎት 11 ቋሚ የማሽነሪ እቃዎች እና
  • ሎት 12 ቋሚ የተገጣጣሚ ዕቃዎች
  • ሎት 13 መስተንግዶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጨረታዉን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ከሎት 1-12 ለተጠቀሱት ዕቃዎች አግባብነት ያለውን ዋና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር የመክፈያ ቁጥር ያላቸው እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

2. የዘመኑን ግብር ከፍለው እንዲሁም በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወርቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 በኮ/ቀ/ክ/ከ/ በወረዳ 07 ቤተል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

  • ሎት 1. 3500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)
  • ሎት 2. 3500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)፣
  • ሎት 3. 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 4. 1500 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር ብቻ)፣
  • ሎት 5. 3000.00(ሶስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 6. 3500 (ሶስት ሺህ አምስት ብር ብቻ)፣
  • ሎት 7. 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ)፣
  • ሎት 8. 1500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር ብቻ)፣
  • ሎት 9. 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ)፣
  • ሎት 10. 3500.00 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)፣
  • ሎት 11. 3500.00 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)፣
  • ሎት 12. ብር 3500፣
  • ሎት 13 .ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የሰነድን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች እያንዳንዱ የሚሸጡበትን ዋጋ እና የጠቅላላዉን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ገቢ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸዉን እና የጨረታ አይነት በመጥቀስ በቤተል አንደኛና ተዘጋጅቶ በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. ተጫራቾችለሚጫረቱት ዕቃ ናሙና ማቀረብ እና አሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ዉልከመፈፀማቸዉ በፊት ቅድመ ብቃት ( የዕቃመጋዘናቸዉን) ለማሳየት ፈቃደኛ መሆን አለባቸዉ።

8. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።

9. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የአሸነፉበትን እቃ 10% የውል ማስከበሪያ CPO ማስያዝ አለባቸው።

10. የሚሰሩ የጥገና ስራዎችን እና የሚፃፉ ፅሁፎችን በተመለከተ ተጫራቾች ቦታው ድረስ በመገኘት ማየት እና መ/ቤቱ በሚሰጠው ዝርዝር መሰረት እንደሚሰሩ አውቀው መሙላት አለባቸው።

11. ተጫራቾች የሚያመጡት መረጃ በአማርኛ ቋንቋ የተተረጎመ መሆን አለበት።

12. ማንኛዉም ተጫራች ከተሰጠው እስፔስፊኬሽን ዉጪ የፃፈ እና ስርዝ ድልዝ ያበዛ በጨረታዉ የማይሳተፍ መሆኑን ማወቅ አለበት።

13. አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከ7 ቀናት በኋላ ዉል መፈፀም የሚችሉ መሆኑን ማወቅ እንዳለባቸዉ እና ግዴታ እንደሆነ አዉቀዉ መሙላት አለባቸዉ።

14. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቤተል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።

15. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ የሚያስገቡት ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30 ይሆናል።

17. ከት/ቤቱ የተሸጠውን ሙሉ የመደበኛ የጨረታ ሰነድ እና የጨረታ መመሪያን በአግባቡ በመሙላት ተመላሽ ማደረግ አለባችሁ።

አድራሻ፡- ዓለም ባንክ ታክሲ ማዞሪያ ትዉልድ ተስፋ ት/ቤት ፊትለፊት

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/07/ት/ት/ፅ/ቤት የቤተል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-19 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bethel Primary and Middle School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T10:31:34.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders