Vehicle

ደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ማህበር የመኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

የመኪና ኪራይ ጨረታ

ደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ማህበር በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች እና አዲስ አበባ ላይ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ በመስራት ላይ የሚገኝ ማህበር ነው። በዚህም የበጎ አድራጎት ማህበራችን የተለያዩ መኪናዎችን ለተለያየ ጊዜ ይፈልጋል ስለሆነም ከሹፌር ጋርም ሆነ ከሹፌር ውጪ ያሉ መኪናዎችን ለማከራየት ፈቃደኛ የሆናችሁ ባለንብረቶች በሙሉ ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የመኪናውን አይነት ከዋጋው እና ከተቋማችሁ አሰራር ጋር በማድረግ እንድታሳውቁን።

የጨረታ መመሪያ፦

  • ተጫራቾች በሚያስገቡት ጨረታ ላይ ተሽከርካሪው የሚገኝበትን ወይም መስሪያ ቤቱ ያለበትን ክልል መጥቀስ ይገባቸዋል።
  • ተጫራቾች ጨረታውን ለመወዳደር ምንም አይነት የCPO ማስያዣ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም።
  • ጨረታውን ለመወዳደር የተሽከርካሪው ሰነድ ህጋዊ መሆን አለበት።
  • ጨረታውን በአካልም ሆነ በኢሜል ([email protected]) ማስገባት የሚቻል ሲሆን ተቀባይነት የሚኖረው ከታች ባለው ሰንጠረዥ አይነት ሙሉ መረጃ የተሟላ ሲሆን ነው።
  • ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ከ28/04/2018 ዓ.ም እስከ 20/01/2019 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

የሚፈለጉት የመኪና አይነቶች

  • Toyota V8
  • Toyota V6
  • Toyota High roof
  • Toyota Coaster
  • Toyota 105
  • Toyota Mark 2
  • Long Base
  • Toyota Deble Pick up
  • Toyota Single pickup
  • Bus (አነስተኛ፣ መካከለኛ)
  • ሌሎችም መኪናዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ሲሆኑ ከመኪናው ሁኔታ አንጻር መሄድ የማይችሉባቸው ክልሎች ላይ ዋጋ ማስገባት ግዴታ አይደለም።

  • ተጫራቾች ለትግራይ፣ ለአፋር፣ ለአማራ፣ ለቤኒሻንጉል፣ ለጋምቤላ፣ ለሱማሌ፣ ለኦሮሚያ፣ ለደቡብ፣ ለሐረሪ፣ ለድሬዳዋ እንዲሁም ለአዲስ አበባ የሚሆን ዋጋ ማስገባት ትችላላችሁ።
  • ተቋሙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • የጨረታ ሰነዱን ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
  • ለበለጠ መረጃና የጨረታ ሰነድ ለማግኘት አድራሻ፦
  • ቦታ፦ መገናኛ ሾላ፣ የካ ፖሊስ መመሪያ ፊት ለፊት፣ እልፍ ፀጋ ህንፃ 4ኛ ፎቅ

የስልክ ቁጥር፦ 0938644444

ደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ማህበር 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-09-15 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Debre Quskwam Charity Organization
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T10:55:17.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders