Others

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ጥገና ስራ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ተቋ 001/2018 ዓ.ም

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ጥገና ስራ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ በጥቃቅን አነስተኛ መብቃት ማህበራትን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል።

ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

ሎት

ራው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ደረጃ

የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን

የጨረታ ማስገቢያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

ሎት 1

የጥገና ስራ

ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ

በጥቃቅንና አነስተኛ መብቃት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት 230-1000 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 230 እስከ 400 ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን 415 ሰዓት ጀምሮ

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

2. በዘርፉ የ2018/19 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና፣ ከስራ ክህሎት ቢሮ የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው።

4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ(Instruction to Bidder(ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይመከራል።

6. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፣ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

7. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን አስፍሮ ማህተም በማድረግ ኤንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በስራ ቀን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እሰከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።

9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው᎓᎓

10. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ ቤተልሐም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

11. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0111 114 800 መረዳት ይችላሉ።

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-25
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 12:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arada Sub City Betelhem Secondary School
  • Bid bond: ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T11:17:47.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders