Sport Materials and Equipment
የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትጥቆችን ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለ1ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ 001/2019
የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትጥቆችን ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡-
በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
ተፈላጊ መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡-
1. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN. NO) ያለው መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፤
2. በሥራው መስክ/በዘርፉ በቀጥታ የተሰማራ እና በበጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸው።
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበና የምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው።
4. ናሙና ከአቀራቢ ድርጅት ሲሆን የዕቃው ዓይነት (Specification) በጨረታው ሠነድ ላይ ግልፅ ይሆናል።
5. ሰነዱን ማግኘት የሚቻለው የማይመለስ የኢት. ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ ያስከፍላል።
6. ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 ፤ ከሠዓት በኋላ 8፡00-11፡00 የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የግዢ ንብረትና ፋይናንስ አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 20 እና 19 በግንባር በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ከጠቀላላ ግዢ ዋጋ 1% በብር ወይም ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ብቻ ከታዋቂ ባንክ አሠርቶ ማምጣት የሚችል።
8. ጨረታውን ካሸነፈ ውል ማስከበሪያ ከግዢው ገንዘብ መጠን ልክ ዐ% ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ከታዋቂ ባንክ የሚያመጣ።
9. የተወዳዳሪዎች ፖስታ፡- አድራሻ፤ ፊርማ፤ የድርጅቱ ማህተም እና ስልክ ቁጥር መኖር፤ እንዲሁም በሰም መታሸግ አለበት።
10, ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. የመወዳዳሪያ ቦታ የኦሮሚያ ወጣቶች ና ስፖርት ቢሮ ግቢ ውስጥ ይሆናል።
12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን አሸንፎ ውል ካልተቀበለ እና ውል ገብቶ ዕቃውን ካላስረከበ የጨረታው ወይም የውሉ ማስያዣ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
13. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ተከታታይ 10 ሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱ ተሽጦ በአስራ አንደኛው ቀን፤ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡30 ላይ በይፋ ይከፈታል።
14. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪ በአካልም ሆነ ህጋዊ ወኪል መወከል ይቻላል፤ ሆኖም ተወዳዳሪ አለመገኘቱ የጨረታውን መክፈቻ አያደናቅፍም።
15. አሸናፊ ድርጅቶች እቃውን ጭነው ቢሮው በሚገኝበት ቦታ ድረስ የሚያመጡ ይሆናል።
16. የቴክኒክ እና የፋይናንሺያል ዶክሜንት ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ መሆን አለበት፤ እንዲሁም CPO የፋይናንሺያል ዶክሜንት ውስጥ መግባት አለበት።
17. ከላይ የተቀመጠው የጨረታው መክፈቻ ቀን በበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ ወደሚቀጥለው ቀን የሚዘዋወር ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0911987001/0911067339 በመደወሰ መረዳት ይቻላል።
አድራሻ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጠመንጃ ያዥ ሰፈር ከእርሻ ሰብል ዋና መ/ቤት ጎን (የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ፊት ለፊት
የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን፤ ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-19 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን፤ ከጠዋቱ 5፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Youth and Sport Bureau
- Buyer address: ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጠመንጃ ያዥ ሰፈር ከእርሻ ሰብል ዋና መ/ቤት ጎን
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T11:38:54.000Z
- Source: 2merkato