Textile, Garment and Leather
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳ 11 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የፊሊጶስ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን እና ተያያዥ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳ 11 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የፊሊጶስ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን እና ተያያዥ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የደንብ ልብስ
- ሎት 2. አላቂ የትምህርት እቃዎችና አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3. የፅዳት እቃዎች
- ሎት 4. ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች
- ሎት 5, የሕትመት ስራ መግዢያ
- ሎት 6. ለጥገና ናእድሳት ስራ
- ሎት 7. ለሚኒስትሪሚንግ መግዣ
ከላይ በተዘረዘሩ ሎቶች ላይ ለምትሳለፉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘረውን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ ይሆናል።
1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 ለተጠቀሱት የተለያዩ ዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች በዘርፉ ሕጋዊ የሆነና የተጫራቹን የስራ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣በታክስ ባለስልጣን የተሰጠ ወቅታዊ የታክስ ክፍያ ሰርተፊኬት፣ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በተጠቀሰው ዘርፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና ከ50,000 ብር በላይ የሚያቀርቡ ድርጅቶች/ግለሰቦች የቫት ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
2.ተጫራቾችዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ማግስትጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 10፡30 ሠዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 ብር (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከት/ም/ቤቱ ግዢ ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በሰንጠረዥ ስር በተቀመጠው ዝርዝር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች መረጃቸውን በአራት ካኪ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) በማድረግ ፋይናሻል ኦርጅናል፤ ቴክኒካልኦርጅናል፤ እና የፋይናሻልና የቴክንካልን ለየብቻው ኮፒ (ቅጂ) ብሎ በመለየት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
|
ሎት |
የእቃው ዓይነት |
ከአጠቃላ ይበጀት % |
ለየሎቱ የሚያሲዘው ሲፒኦ |
|
1 |
የደንብ ልብስ |
0.5% |
7000 ብር |
|
2 |
የጽዳት እቃዎች |
0.5% |
5000 ብር |
|
3 |
አላቂ የት/ምና የቢሮ ዕቃዎች |
0.5% |
9000 ብር |
|
4 |
ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች |
0.5% |
7000 ብር |
|
5 |
የሕትመት ስራ መግዢያ |
0.5% |
4000 ብር |
|
6 |
ለጥገና ና እድሳት ስራ |
0.5% |
7000 ብር |
|
7 |
ለሚኒስትሪሚንግ መግዣ |
0.5% |
4000 ብር |
5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም። እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነድ ላይ በየገፁ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ ግዴታ ነው።
6.በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጀተው በጨረታው መሳተፍ የሚፈጉ ተጫራቾች የራሳችሁን እሴት ያልጨመራችሁ እና አምራች ያልሆናችሁ እንደማን ኛውም ተወዳደሪ የጨረታ ሰነድ 300 ብር (ሶስትመቶብር) በመክፈል እና ሲፒኦ በማሲያዝ መወዳደር ትችላላችሁ። አምራች የሆናችሁ ከአደራጃችሁ ተቋም የትምህርት ቤታችንን ስም እና የጨረታውን ቁጥር ጠቅሰው በማፃፍ በተገለፀው መሰረት የእቃውን ወይም የአገልግሎቱን አይነት የሚገልፅ የዋስትና ደብዳቤ እና የአምራችነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው። በተባለው መሰረት ካላቀረቡ የማናስተናግድ መሆኑንን ከወዲሁ እናሳውቃልን። እነዚህን በማቅረብ መሳታፍ ይችላሉ።
7.ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ (CPO) 10% ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
8.የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት ታሸጎ በዛው ዕለት 4፡30 ሠዓት በት/ቤቱ ቤተመፅሃፍ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት ። እንዲሁም የሚከፈትበት ቀን ካላንደር የሚዘጋውና ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ሀገር አቀፍ ክብረ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
9. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎቶች ላይ ናሙናዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
10. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት አይኖረውም።
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በውሉ መሰረት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ግዴታ አለበት።
12. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን አይነት መግለጽ ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ወረዳ 11 ት/ት ጽ/ቤት ከአጠና ተራ ወደ ሱሚ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ከሙስሊሞች መቃብር ፊት ለፊት የፊሊጶስ የመጀ/ደ/ት/ቤት
ስልክ 0112738932
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የፊሊጶስ አፀደ ህፃናት እና የመጀመያ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-09-19 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Philipos Kindergarten & Elementary School
- Buyer address: ኮልፌ አጠና ተራ ፌሊጶስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T11:52:29.000Z
- Source: 2merkato