Textile, Garment and Leather
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የተለያዩ ለሰራተኞች ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ አልባሳት፣ ጋዋን፣ ቆዳ ጫማ፣ ቦቲ ጫማ፣ ሴፍቲ ጫማ፣ ዶከተር ሹዝ እና ሹራብ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
ድርጅታችን የተለያዩ ለሰራተኞች ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ አልባሳት፣ ጋዋን፣ ቆዳ ጫማ፣ ቦቲ ጫማ፣ ሴፍቲ ጫማ፣ ዶከተር ሹዝ እና ሹራብ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች
1. የታደሰ ፍቃድና የዘመኑ ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
2. የማይመለስ ቫትን አካቶ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ገንዘብ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
3. ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት።
4. ለጨረታ ዋስትና የሚሆን የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ለብቻው በኤንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
5. ተጫራቾች ዋጋ ላቀረቡባቸው የተለያዩ የሥራ መገልገያዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤
6. የጋዋን፣ ቴትሮን ሸሚዝ፣ ካኪ ቴትሮን ሸሚዝ፣ ካኪ ቱታ፣ ቴትሮን ቀሚስ ላይ የምትወዳደሩ ደንበኞች ደረት ላይ 2019 ዓ.ም የሚል ፅሁፍ ማካተት የሚችል፣
7. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፖ.ሳ.ቁ. 3516
ስልክ 011 369 0563 ፋክስ 011 5 513299
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-10-08
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-08 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: National Alcohol and Liquor Factory (NALF)
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T11:54:54.000Z
- Buyer website: https://www.nalf.com.et
- Source: 2merkato