Textile, Garment and Leather

የካ አባዶ ቅ/መ/የመ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የአንደኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የካ አባዶ ቅ/መ/የመ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተቀመጡትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተቀመጠው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  • ሎተ 1፤ የተለያዩ ደንብ ልብሶች
  • ሎት 2፡አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 3፤ አላቂ የህክምና እቃዎች
  • ሎት 4፡አላቂ የት/ት እቃዎች
  • ሎት 5፡ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 6፡ ሌሎች አላቂ መሳሪያዎች
  • ሎት 7፡ ለፕላንት ማሽነሪ እድሳትና ጥገና
  • ሎት 8፡ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት
  • ሎት 9፡ ለቋሚ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 1ዐ፡ የፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ
  • ሎት 11፡ ለልዩ ልዩ ክፍያዎች

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃዎን እና ቲን ነምበር በወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ካሽ ሪጅስተር ማሽን ያላችሁ /ከሌላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ማለትም በምን ምክንያት እንዳላወጡ የሚገልፅ ደብዳቤ እና ከብርሃንና ሰላም የታተመ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑና የተጠየቁትን ሁሉ ካላሟሉ መወዳደር የማይችሉ መሆንዎን እናሳውቃለን ፤

3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን

4. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የምትሰሩ ድርጅቶች የምታመጡት የጨረታ ማስከበሪያ ድብዳቤ በሀላፊ የተፈርመ መሆን አለበት፡፡ ሰነዱ የሚሸጠው ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የካ አባዶ ቅ/መ/የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ሎት 1. የተለያዩ ደንብ ልብሶች(6211) 20000 ብር፣ ሎት -2 (አላቂ የቢሮ እቃ(6212) 20000 ብር፤ ሎት 3 የህክምና እቃዎች(6214) 5000 ብር ፣ሎት 4 አላቂ የት/ት እቃዎች (6215) 15000፤ ሎት 5 ፡የጽዳት እቃዎች (6218) 15000፣ ሎት 6፡ ሌሎች አላቂ መሳሪያዎች( 6219) 15000፣ ሎት 7፡ ለፕላንት ማሽነሪ እድሳት ጥገና (6243) 25000፣ ሎት 8፡ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት (5000)፣ ሎት 9፡ ለቋሚ የቢሮ እቃዎች( 20000)፣ ሎት 10 የፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ / 6313/ 30000 እና ሎት 11፡ ለልዩ ልዩ ክፍያዎች(5000) ለተዘረዘሩት ሎቶች ሁሉ በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ለመወዳደር የስራውን/ እቃውን ዋጋ ከቫት ጋር ደምረው ያስገቡ፡፡

6. ተጫራቾች ለስራው የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ ፖስታውን በማሸግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

7. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው በወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት /በዓል ከሆነ/ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 14 የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ሳይት ውስጥ የካ አባዶ ቅ/መ/የመ/ደ/ት/ቤት ወይም ከካራ ወደ ጣፎ ሲሄዱ በገደራ ሳራ አንፑል በግራ በኩል 1000 ሜትር ገባ ብሎ የየካ አባዶ ኮንዶምንየም ሳይት ውስጥ

ማሳሰቢያ ፡

1. ተወዳዳሪው አንድ ኦርጅናል የያዘ ፖስታ አንድ ኮፒ የያዘ ፖስታ እና አንድ ሲፒኦ የያዘ ፖስታ ማቅረብ አለበት፡፡

2. አሸናፊው ድርጅት ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት የጨረታው ዋጋ 10% በ/ሲ.ፒ.ኦ/ በቼክ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ካላቀረቡ ትዕዛዝ የማይሰጥ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

3. ፖስታው ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተም ከሌለው አይከፈትም፡፡

አዲስ አበባ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0925 399 344

የካ አባዶ ቅ/መ/የመ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-19 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት /በዓል ከሆነ/ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Abado Kindergarten & Elementary School
  • Buyer address: ለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 14 የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ሳይት ውስጥ የካ አባዶ ቅ/መ/የመ/ደ/ት/ቤት ወይም ከካራ ወደ ጣፎ ሲሄዱ በገደራ ሳራ አንፑል በግራ በኩል 1000 ሜትር ገባ ብሎ የየካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ሳይት ውስጥ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T12:07:19.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders