Textile, Garments and Uniforms

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የሰራተኞች የደምብ አልባሳት፣ የሰራተኞች የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች (PPE)፣ የፅዳት እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች እና የተለያዩ ተሸከርካሪ ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሰነድ ቅጽ

የብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁፕር APPF/NCB/02/19

  1. በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
    • LOT 1.የሰራተኞች የደምብ አልባሳት
    • LOT 2. የሰራተኞች የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች (PPE)
    • LOT 3. የፅዳት እቃዎች
    • LOT 4. የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች
    • LOT 5. የተለያዩ ተሸከርካሪ ጎማዎች
  2. ተጫራቾች የስራ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለሚከፈልባቸው ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሰርተፊኬት እና በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ፖርታል ላይ በአቅራቢነት መመዝገቡን የሚያሳይ መረጃ እንደ ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ይኖባቸዋል።
  3. ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኢምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኢምባሲ ፊት ለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመክፈል ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስምና አድራሻ በትክክል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦሪጅናሉን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን እስከ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መክፈቻው እለት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ርዋንዳ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል።
  9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ኢአ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር 011 662 4656 አ/አ፣ አዳሚ ቱሉ 0464419164 (ማዞሪያ)፤

0464419287 (ንግድ መምሪያ) ፓ.ሣ.ቁ 1206 (አ.አ)፣ 247 (አ/ቱሉ)

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን

አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-24 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Adami Tulu Pesticides Processing Factory
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T12:39:23.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders