Accounting and Auditing, Accounting System Design
የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን የ2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም. በጀት ዓመታት የፋውንዴሽኑን የፋይናንስ ሪፖርቶችና የሒሳብ መግለጫዎች/በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል
Description
የውጭ ኦዲተር የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን የ2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም. በጀት ዓመታት የፋውንዴሽኑን የፋይናንስ ሪፖርቶችና የሒሳብ መግለጫዎች/በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች የድርጅታቸውን መግለጫ፣ የሕጋዊ ምዝገባና የሙያ ፈቃድ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ አስፈላጊውን የግብር ማረጋገጫ፣ በተመሳሳይ የኦዲት ሥራ ያላቸውን ልምድ የሚያረጋግጡ ሰነዶችን እንዲሁም የሙያ ብቃት መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
በተጨማሪም የኦዲት ሥራውን አፈጻጸም የሚያብራራ የቴክኒክ ፕሮፖዛል፣ የኦዲት ክፍያን የሚያሳይ የፋይናንስ ፕሮፖዛል፣ የሥራ ዕቅድና የሥራውን የማጠናቀቂያ ጊዜ የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚፈለጉትን ሰነዶች በማሟላት የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛሎቻቸውን በታሸገ ሁኔታ በዱራሜ ከተማ ለሚገኘው ለዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ከታች ባለው የኢሜይል አድራሻ እንድታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ 0916276399 ወይም በኢሜይል አድራሻ [email protected] ማግኘት ይቻላል። ከተገለጸው የመጨረሻ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ ፕሮፖዛሎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። የተመረጠው ኦዲተር የኦዲት ሥራውን ከውል በኋላ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።
ፋውንዴሽኑ የቀረቡትን ፕሮፖዛሎች በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት የመገምገምና ተገቢውን ኦዲተር የመምረጥ መብቱን የጠበቀ ሲሆን፣ ማንኛውንም ፕሮፖዛል በሙሉ ወይም በከፊል የመቀበል ወይም ያለመቀበል መብቱም የተጠበቀ ነው።
የኦዲት ሥራው መሰን
የተመረጠው የውጭ ኦዲተር የፋውንዴሽኑን የፋይናንስ ሪፖርቶች፣ የገቢና ወጪ ሂሳቦች፣ የባንክ ሂሳቦች፣ እንዲሁም ተያያዥ የሒሳብ መዝገቦችና የፋይናንስ ሰነዶችን በተፈጻሚው የኦዲት ስታንዳርድ መሠረት በመመርመር የፋይናንስ ሪፖርቶቹ ትክከለኛነትና ተገቢነት ላይ የኦዲት አስተያየት ይሰጣል። ኦዲቱን ከጨረሰ በኋላ የኦዲት ሪፖርት የሚያቀርብ ሲሆን፣ በኦዲቱ ወቅት የታዩ የፋይናንስ አሠራር፣ የውስጥ ቁጥጥር ወይም ሌሎች የማሻሻያ ጉዳዮች ካሉ ተገቢውን የማሻሻያ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።
የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-09-12 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን
- Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T12:56:54.000Z
- Source: 2merkato