Accounting and Auditing, Accounting System Design
ታክሲዬ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/ኅ/ስ/ማህበር የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ኦዲት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል
Description
ለኦዲት አገልግሎት የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
ታክሲዬ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/ኅ/ስ/ማህበር የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ኦዲት በህግ በተደነገገው መሰረት ኤዲት ለማስደረግ ብቁ የሆኑ የውጪ ኦዲተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. መስፈርቶች
- ፈቃድ፦ የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) ማረጋገጫ ያለው/ያላት።
- ብቃት:- በህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ እና መመሪያ መሰረት ኦዲት ለማድረግ ብቁ የሆነ/ የሆነች።
- ልምድ፦ በተመሳሳይ ተቋማት የኦዲት ስራ ቢያንስ 4 ዓመት ልምድ ያለው/ያላት
- ህጋዊነት: የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር የከፈለ/የከፈለች።
- ነጻነት ከማህበሩ ጋር የጥቅም ግጭት የሌለበት፣ የማህበሩ ቦርድ አባል እና ሰራተኛ ያልሆነ /ያልሆነች።
- የኦዲት ሪፖርት እና አስተያየት (ማናጅመንት ቁጥጥር) ማቅረብ የሚችልና የኦዲት ሪፖርቱን ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ማጸደቅ የሚችል/የምትችል።
2. የሚፈለጉ ሰነዶች
- የንግድ ፈቃድ፣ የሙያ ፈቃድ፣ TIN ኮፒ፣
- ቴክኒካል ፕሮፖዛል (የስራ እቅድ እና የጊዜ ሰሌዳ)።
- ፋይናንሻል ፕሮፖዛል (ዋጋ እና የአከፋፈል ሁኔታ)።
- የባለሞያዎች የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ።
- የቀድሞ ስራዎችን የሚገልጽ ማጣቀሻ ምስከር ወረቀት።
3. የጨረታ አቀራረብ
- የመጨረሻ ቀን:- ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት።
- ማቅረቢያ ቦታ፡- አዲስ አበባ የረር ጎሮ አለማየሁ ህንጻ ፊት ለፊት አሊና ህንጻ 1ኛ ፎቅ የማህበሩ ዋና ቢሮ።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፦ 09 96030303/09 94 23 23 23 ይደውሉልን።
ደርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
ታክሲዬ የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ኃላ/የተ/ኅ/ስ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-11-14
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት
- Bid opening: 2026-11-14 17:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ታክሲዬ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/ኅ/ስ/ማህበር
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T08:27:48.000Z
- Source: Qelal Tenders