Accounting and Auditing, Accounting System Design
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን ከ 2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት (እ.ኢ.አ የ2017፣ የ2018 እና የ2019) የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ለማሠራት ይፈልጋል
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ
በግዥ መለያ ቁጥር፡ ERTE/NCB/Serv/003/2019
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን ከ 2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት (እ.ኢ.አ የ2017፣ የ2018 እና የ2019) የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ለማሠራት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በግልፅ ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው።
1. ከሚመለከተው አካል በዘርፉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የወሰደና የታደሰ፤
2. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት፤ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተቀባይነት ያለው የግብር ክሊራንስ (ታክስ ክሊራንስ) በአቅራቢነት (EGP) ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ወይም ሕጋዊ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችል።
4. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የፋይናንስ ዲፓርትመንት መግዛት ይችላሉ።
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ይከፈታል፤ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይሆናል፣
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅቱ የሥራ ሰዓት
- ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት - 6፡00 ሰዓት
- ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት – 11፡00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ እስከ 10፡00 ሰዓት
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ሕንፃ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር 011 439 0075 / 1569 / 3592 / 011 439 1027
ፋክስ 011 439 6336 ፖ.ሳ.ቁ. 2562
አዲስ አበባ
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-11-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-17 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Elet Derash Relief Transport Enterprise
- Buyer's registered address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንፃ ጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T08:38:21.000Z
- Source: Qelal Tenders