Accounting and Auditing, Accounting System Design
ኤም ቪ አር ኮንሰልቲንግ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በአባይ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር የሚገኙ ድርጅት (ኩባንያ) የ2018 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኤም ቪ አር ኮንሰልቲንግ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በአባይ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር የሚገኙ ድርጅት (ኩባንያ) የ2018 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላሉ።
- የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የሙያ እና የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- የአገልግሎቱ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከኢትዪጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ካደረጋቸው ኩባንያዎች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በኩባንያው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ከኩባንያው በመግዛትና መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ” የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 302 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ መስከረም 12/2019 ዓ.ም ከረፋዱ በ3፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን ከረፋዱ 4፡00 በኩባንያው ቢሮ ቁጥር 302 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) ድርጅቶች በሚገኙበት ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቃችሁ የምትሳተፉ፡፡
| ተ.ቁ | ሎት | የጨረታ ማስከበሪያ | አድራሻ |
| ሎት 1 | |||
| 1 | ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| 2 | ኤ.ጂ ፓይፕ ፊቲንግ ቴክኖሎጂ | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| ሎት 2 | |||
| 1 | የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| 2 | የቤት ልማት ድርጅት | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| ሎት 3 | |||
| 1 | ሕብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| 2 | አማራ ፓይፕ ፋብሪካ | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| ሎት 4 | |||
| 1 | የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| 2 | ደን ኢንተርፕራይዝ፡፡ | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| ሎት 5 | |||
| 1 | ጎሽ ሜዳ ፓይፕ እና ፕላስቲክ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ፡፡ | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
| 2 | ልህቀት ዲዛይን እና ሱፐርቪዥን ወርክስ ኢንተርፕራይዝ፡፡ | 2 በመቶ | ባህር ዳር |
ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 226 51 12 ወይም 058 222 22 30 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ። አድራሻ አምባሰል ንግድ ስራዎች 3ተኛ ፎቅ ባሕር ዳር ከተማ ይገኛል።
ኤም ቪ አር ኮንሰልቲንግ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-09-22 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: MVR CONSULTING GROUP PLC
- Buyer TIN: 0041199649
- Bid bond: 2% በየሎቱ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T13:26:11.000Z
- Source: 2merkato