Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የፅዳት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/04/2019

  1.  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የፅዳት አገልግሎት ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሸሪ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000/አንድ ሺ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ሕዳሴ ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 114 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የዕዳት አገልግሎት ግዥ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/04/2019 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር ብቻ) ለ60 (ስልሳ) ቀናት የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6.  ጨረታው መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሕዳሴ ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡
  7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 11 መደወል ይችላሉ ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-21 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 09, 2026)
  • Posted at: 2026-09-09T09:23:53.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders