Vehicle and Machinery Sale
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ መለያ ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/03/2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/02/2026 በግልጽ ጨረታ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በድጋሚ ግልጽ ጨረታ የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ከማሽነሪዎቹ የአገልግሎት ባህሪ መሰረት ተጫራቾች ከንዑስ ክፍል 1-3 ያሉት ላይ ለመሳተፍ ከእያንዳንዱ ከፍል ቢያንስ አንድ ማሽነሪ ላይ መጫረት ግዴታ ሲሆን፤ በቀሪዎቹ ከንዑስ ክፍል 4-6 ያሉት ላይ ግን በተናጠል ወይም በጅምላ እንደፍላጎታቸው ለመሳተፍ።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
1. ተጫራቾች የታደሰ የቀበሌ/የፋይዳ መታወቂያ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የቀረጥ ነጻ መብት ያላቸው ወይም ቀረጥ ከፍለው መስተናገድ የሚፈልጉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የሚሳተፉበትን የማሽነሪዎች ድምር ዋጋ 25% (ሀያ አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በጨረታው ዕለት ይዘው መቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በባንኩ 3ኛ ህንጻ 2ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል።
4. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት፣ ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
5. የተዘረዘሩትን እቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በአስር (10) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪ ያያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
6. ማሽነሪዎቹን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ገላን ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ዕቃዎች ግዢና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር፡ +251-11 524-4490 ወይም ኢ-ሜይል: [email protected] መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-10-06
- Bid closing time: 09:00
- Bid opening: 2026-10-06 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Sep 10, 2026)
- Posted at: 2026-09-10T07:57:34.000Z
- Source: 2merkato