Equipment and Accessories

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሰነድ ቁጥር 130

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ቁሳቁሶቹም፦

  1. ያገለገሉ ጎማዎች
  2. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  3. ያገለገሉ የስፖንጅ ፍራሾች
  4. የብረት ገዳዎች (ዲፖዎች)፤ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ቶቦላሬዎች ስክራፕ/
  5. የተነቃቀሉ ጣውላዎች
  6. የማካሮኒና የፓስታ መጠቅለያ ማሽንና ጀኔሬተሮች
  7. ያገለገሉ ወንበሮች

በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰቢያ

  • ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 89-90-90-51 ወይንም 09 75-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-21 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mekedonia Charity Association
  • Buyer TIN: 0027054421
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T07:57:09.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders