Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ስር የሚገኘው እሸት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ስር የሚገኘው እሸት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የ2019 ዓ.ም. ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡ -የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት፣
  • ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት 3፡- አላቂ የትምህርትና
  • ሎት 4፡- የህትመት ስራዎች፣ 
  • ሎት 5፡- የህክምና እቃዎች
  • ሎት 6፡- የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 7፡- የማሽነሪ ጥገና
  • ሎት 8፡- ቋሚ ዕቃዎች

በጨረታው መሳተፍ የምትፈለጉ ህጋዊ ተጫራቾችና ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡-

  • የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ።
  • የ2018 ዓ.ም. የታደሰ ንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር TIN/ የተሰጠው።
  • ተጫራቾች QR CODE ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።
  • በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ የአቅራቢነት ዝርዝር /supplier list/ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ዝርዝር ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀና ለእያንዳንዱ ናሙና የሚቀርብበትን ማቅረብ የሚችል በተጨማሪም በፎቶግራፍ የሚቀርብበትን ማቅረብ ይኖርበታል።
  • በጨረታ መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ የጨረታ ተሣትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  • ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከእሸት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማድረግ አለበት።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ የአንዱን ዋጋ ቫትን አካቶ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎኘ ፖስታ ዋና እና ኮፒውን በመለየት ቴክኒክና ፋይናንሺያሉን አንድ ላይ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ እሸት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በፋይናንስ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
  • ማንኛውም ተጫራቾች መጫረት የሚችለው በሚመለከታቸው የንግድ ሰራ ፍቃድ የስራ ዘርፍ፣ ብቻ ነው።
  • ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች የምትወዳደሩበትን የራሣችሁን ምርትና ዕቃ አምራች መሆናችሁን የሚገልፅና በአመረታችሁበት ዕቃ ላይ የምትወደደሩ መሆኑን እናሣውቃለን።
  • አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፋትን ዕቃ በራሣቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ድረስ ማድረስ አለባቸው። በተጨማሪም ት/ቤቱ የሚገዙትን ዕቃዎች ላይ እንደአስፈላጊነቱ 20% የመጨመር ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ተጫራቾች ያሸነፋትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ሁሉም የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ሁለት ቀን በፊት ሣምፕል ማቅረብ አለባቸው፡ ሣምፕል ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል። እንዲሁም ዋጋቸውን ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት። ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ኑው።
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎቶች የተጠቀሰውን ብር በ0.5% የተሰራ ሲሆን
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎቶች CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል። 
  • የአካውንት ቁጥር ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ሎት

 

ሎት 1

 

ሎት 2

 

ሎት 3

 

ሎት 4

 

ሎት 5

 

ሎት 6

 

ሎት 7

 

ሎት 8

 

ብር

7,500.00

 

5,000.00

2,900.00

5,000.00

 

240.00

65,000.00

 

1,600.00

 

7,500.00

 

ማሳሰቢያ፡-

  • የዘገየ ጨረታና በመክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
  • የግዥ ሰነድ አንድ ላይ ተያይዞ መመለስ አለበት
  • የእቃ ሣምፕል የምንቀበለው ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ድረስ ነው
  • ት/ቤቱ የተጫራቾች ውጤት ከገለፀበት ቀን ጀምሮ በሰባት ቀናት ውስጥ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ፣

  • አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኳስ ሜዳ ከሸዋ ፀጋ ህንፃ 100 ሜትር ከፍ ብሎ
  • ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል ወይም ስልክ ቁጥር 0112 77 59 49/50 ደውለው ያነጋግሩ

እሸት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-09-23 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Eshet Kindergarten and Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T08:14:19.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders