Stationery
በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለካምፓሱ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎች፡ ኬሚካሎችን እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለካምፓሱ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎች፡ ኬሚካሎችን እና ቋም ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1. ለተጠየቁት ዕቃዎች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላችሁ ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በካምፓሱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመቅረብ ሰነዱን 500.00 /አምስት መቶ/ ብር ባንክ ገቢ በመድረግ በግዥ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለይ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ጠዋት 3:00 ሰዓት ማቅረብ እና ሳጥን መስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካምፓሱ አዳራሽ ይከፈታል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የተወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ(C.PO) ለኤሌክትሮኒክስ፡ ፅህፈት መሳሪያ እና ፅዳት ዕቃዎች ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ/ ለጎማ፡ ለፈርኒቸር እና ኬሚካል ሰነዶች ብር 30,000.00/ሰላሣ ሺህ/ በካምፓሱ ስም በማስያዝ ማቅረብ ይኖርበታል።
5. አሸናፊው ተጫራች አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና ዕቃዎቹን ከካምፓሱ በሚሰጠው ፕሮግራም መሠረት በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ በሚገኘው ካምፓስ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
6. ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0930107417(0911742980)ይጠይቁ።
በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰሳ ካምፓስ
Tender details
- Deadline: 2026-09-29
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-29 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Oromia State University
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T08:22:46.000Z
- Source: 2merkato