Textile, Garment and Leather
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 08 ክልል የሚገኘው የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት እና የጭነት እና ለመዝናኛ ክበብ አገልግሎት የጥገና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል
More tags
Description
የመጀመሪያ ዙር የግልፅ የጨረታ መመሪያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 08 ክልል የሚገኘው የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 001/2019 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት እና የጭነት እና ለመዝናኛ ክበብ አገልግሎት የጥገና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ሎት1. የደንብ ልብስ ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት3. ህትመት ሎት4. የሕክምና እቃዎች ሎት5. የፅዳት እቃዎች ሎት6.የተለያዩ መፅሕፍት ሎት7. የላብራቶሪ እቃዎች ሎት8. ቋሚ እቃዎች ሎት9. የስፖርት መገልገያ ሎት10. ልዩ ልዩ መገልገያዎች ሎት11. ለጭነትና ለጉልበት ሎት12. ለመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሎት13.ማሽነሪ ጥገና እና ሰርቪስ ሎት14. የተገጣጣሚ እድሳት እና የህንፃ ጥገና ስራዎች
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ድርቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው
2. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
3. ተጫራቾች ይህን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት በየሎቱ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሽገ የድርጅታቹን ማህተም ያረፈበት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
5. ጨረታው በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዲሁም ከአደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱ በጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በግልፅና በዝርዝር በተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ከአስተባባሪ የተፈረመ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታ ማስረከቢያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን ሎት1፡35,000 ሎት2፡- 35,000 ሎት3፡ 5,000 ሎት4፡1,200 ሎት5፡-20,000 ሎት6፡6,000 ሎት7፦12,500 ሎት8፡- 60,000 ሎት9፡12,500 ሎት10፡- 6,000 ሎት11፡- 9000 ሎት12፡- 30,000 ብር ሎት13፡- 3,000 ሎት14፡- 14,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማቅረብ አለባችሁ፡፡
8. በጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘውን ሲፒኦ በመውሰድ እና ተጫራቾች ውል እንዲዋዋሉ ከመ/ቤቱ ሲገለፅላቸው ያሸነፉበትን የዋጋ ድምር 10% በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከተውን የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
10. ጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውጭ በጥራት የሚበልጥና የሚስተካከል ዋጋ ያለው ዕቃ በማቅረብ መወዳደር ይቻላል፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው በጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫ 2ኛ እና 3ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል፡
12. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡባቸው የተመረጡትን ዕቃዎች ናሙና እስከ ግልፅ ጨረታ ማለቂያ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ተጫራቾች ከት/ቤቱ የወሰዳችሁትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በናንተ የሚሞሉ ክፍሎችን በመሙላት ተመላሽ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
14. አንድ ተጫራች ሌላው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
15. ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኙ ጨረታውን ከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በጦርኃይሎች በሆላንድ ኤንባሲ ወደ ቀራንዮ አደባባይ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ በኩል ፍላንስ ጋር
ስልክ ቁጥር፡- 011-8-33-69-84
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-24 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Keranio Medihanialem No.2 Elementary School & Middle School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T08:31:56.000Z
- Source: 2merkato