Textile, Garment and Leather

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ቤት የኮከበ ፅባህ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የት/ዘመን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ቤት የኮከበ ፅባህ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ ና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የት /ዘመን ለ2ኛ ዙር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ሎት 1 የደንብ ልብስ፤ ሎት2 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3 ህትመት ሎት 4 የህከምና እቃዎች ሎት 5 የትምህርት እቃዎች ፤ ሎት6 የፅዳት እቃዎች ሎት7 የጥገና ዕቃዎች ሎት8 የቋሚ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ተጋብዛችኋል።

1. በዘርፉ አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ያላቸው።

2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO.) ያላቸው ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ። ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል እና ሰነዱን በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ፤ የሚጫረቱበትን አይነት ፤ ለእያንዳንዱ ሎት ሎት 1 የደንብ ልብስ፦ 16,000.00 /አስራ ስድስት ሺህ ብር ሎት2 የፅህፈት መሳሪያ፡- 9,000.00/ዘጠኝ ሺህ ብር ሎት 3 ህትመት፡- 570.00/አምስት መቶ ሰባ ብር ሎት 4 የህክምና እቃዎች ፡- 500.00/ አምስት መቶ ብር ሎት 5 የትምህርት እቃዎች - 17,000.00/ አስራ ሰባት ሺህ ብር፤ ሎት6 የፅዳት እቃዎች፡- 18,000/ አስራ ስምንት ሺህ ብር፣ ሎት 7 የጥገና እቃዎች 13,000.00/ አስራ ሶስት ሺህ ብር፤ሎት8 የቋሚ እቃዎች፡- 13,500.00/አስራ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውልና በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሳጥኑ ታሽጎ ወዲያዉ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታው ሳጥን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሲያስገቡ በአንድ ኦርጅናል ና ኮፒ ለየብቻ ኦርጅናል እና ኮፒ ተጠቅሶ መባል ይኖርበታል።

8. የጨረታው ሰነድ የሚሞላው በተቋሙ ሰነድ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡ ተጫራቹ በራሱ ሰነድ ላይ ከሞላ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

10. ተጫራቾች ተወዳድረው ባሸነፉበት እቃዎች ላይ 10 ፐርሰንት ማስያዣ ይኖርባቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ኮከበ ፅባህ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ ና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቀበና ራሺያ ኤንባሲ ጎን

ስልክ ቁጥር 0116 585 320

የኮከበ ፅባህ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ ና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውልና በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-09-23 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውልና በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kokebe Tsebah Kindergarten and Primary School
  • Buyer address: ኮከበ ፅባህ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ ሲመጡ ቀበና አደባባይን እንደተሻገሩ ኮከበ ፅባህ መሰናዶ ት/ቤት ጀርባ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T08:49:48.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders