Equipment and Accessories
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. የተለያዩ ማሽነሪዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች ለመሸጥ ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsMechanical
Addis Ababa
More tags
Industrial Machinery Provision and InstallationOther SalesSales, Disposals and ForeclosureVehicle and Machinery SaleVehicle and Machinery ForeclosureMachinery and EquipmentAgriculture and FarmingWater Engineering Machinery and EquipmentConstruction and Water WorksConstruction Machinery and EquipmentAmharic2merkatoAddis Capital Goods Finance Business S.C
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
የሐራጅ መለያ ቁጥር 01/2018
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ የተለያዩ ማሽነሪዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት መሳትፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች ኩባንያው የተለያዩ 80 ማሽነሪዎች በሐራጅ የሚሸጥ ሲሆን የማሽኖቹን ዝርዝር ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የሐራጅ ሽያጭ ሰነድ ላይ የሚያገኙ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያም የሚወዳደሩበትን የማሽን አይነቶች ጠቅላላ የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባችኋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች ማሽኖቹን ኩባንያው በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት በአካል ተገኝተው ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው በመቅረብ ከጨረታው ቀን በፊት መጎብኘት ይኖርባቸዋል።
- በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመካሄዱ ከጠዋቱ 4፡30 በፊት ባለው ጊዜ ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል። ሐራጁ በቀን 19/1/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው መጋዘን የሚካሄድ የሆናል።
- ሐራጁ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት በኩባንያው መጋዘን ውስጥ ይካሄዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስ⁄ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ 200 ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የሐራጅ ጨረታው ከተካሄደበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ለኩባንያው አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ክፍያውን በፈጸመ በ10 ቀናት ውስጥ ማሽኖቹን ማንሳት አለበት።
አድረሻ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተሻግሮ የ6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው የኩባንያው ህንፃ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-217 9967 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-09-29
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-09-29 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Capital Goods Finance Business S.C
- Buyer address: Arat Kilo next to Tourist hotel Ethiopian Post service organization building 3rd floor, procurement administration directorate office
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T08:56:00.000Z
- Source: 2merkato