Textile, Garment and Leather
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከ/ከተማ በወረዳ 03 የብርሃንህ ዛሬ የቅደመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የ2019 ዓ/ም 1ኛዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 001/2019ዓ/ም
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከ/ከተማ በወረዳ 03 የብርሃንህ ዛሬ የቅደመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ከዚህ በታት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት 1 የደንብ ልብስ ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት 3 የህትመት ስራ ሎት 4 የህክምና ዕቃዎች ሎት 5 አላቂ የት/ት ዕቃዎች ሎት 6 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች ሎት 7 የቋሚ ዕቃ ኤሌክትሮኒክስ ሎት 8 ቋሚ ዕቃ የቢሮ ተገጣጣሚ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያማሉ መሆን አለባቸው።
ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
ባጀት ኮድ |
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
6211 |
የደንብ ልብስ |
14,866.00 |
|
ሎት 2 |
6212 |
የአላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
9,200.00 |
|
ሎት 3 |
6213 |
የህትመት ስራዎች |
1,700.00 |
|
ሎት 4 |
6214 |
የህክምና ዕቃዎች |
1,100.00 |
|
ሎት 5 |
6215 |
የአላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
15,000.00 |
|
ሎት 6 |
6218 |
የአላቂ ሌሎች የፅዳት ዕቃዎች |
12,300.00 |
|
ሎት 7 |
6313 |
የቋሚ ዕቃ ኤሌክትሮኒክስ |
12,600.00 |
|
ሎት 8 |
6314 |
ቋሚ ዕቃ የቢሮ ተገጣጣሚ ዕቃዎች |
12,650.00 |
1. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጡ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጨማሪ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5. ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ c.p.o ሲ.ፒ.ኦ በእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው መሰረት ማቅረብ አለባቸው። ጥቃቅንና አነስተኛ የተዳራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል መደራጀታቸው በጨረታ ዋስትና ስራ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
6. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎት የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 6 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የዕቃውን ናሙና ዝርዝር የግዥ ንብረት አስተዳደር ክፍል ገቢ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው አንድ ወጥ የሆኑ ዋናና ቅጂ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ብርሃንህ ዛሬ ቅ/መ እና የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስና ግዥ ንብረት አስተዳደር ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንህ ዛሬ የቅ/መ እና የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው
11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያማሉ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል።
13. ት/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ለጨረታ የተሰጠው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ይሆናል።
15. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
16. አሸናፊው ድርጅት የግዥ ትዕዛዝ /our chase order/ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ እና የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ላይ ያሉ መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ብርሃንህ ዛሬ /የመ/ደ/ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
17. አማራጭ ጨረታ አይፈቀድም ግዥ ፈፃሚው
18. የታወቁ ጉዳቶች የካሳ ክፍያ የገንዘብ መጠን በቀን 0.1% ይሆናል።
19. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ብርሃንህ ዛሬ ቅ/መ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ክፍያና ሂሳብ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በማቅረብ ወይም በስልክ 011 61 89 961 ወይም 011 66 73 407 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡ 22 ማዞሪያ ጌታሁን ባሻህ ህንፃ 500 ሜትር ገባ ብሎ
የብርሃንህ ዛሬ የቅደመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-23 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የብርሃንህ ዛሬ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር በየሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T08:59:04.000Z
- Source: 2merkato