Chemicals and Reagents
የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር-01/2019
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኛው የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
የሎት ቁጥር |
የአገልግሎት አይነት |
የሚያስይዙት የገንዘብ መጠን በCPO |
|
ሎት 1 |
መድሃኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ |
30,000 |
|
ሎት 2 |
የህክምና መገልገያ ቋሚ እቃ |
30,000 |
|
ሎት 3 |
የስራ መገልገያ የደንብ ልብስ ግዢ እና የደንብ ልብስ ስፌት |
20,000 |
|
ሎት 4 |
የፅህፈት መሳሪያ እና አላቂ የፅዳት እቃዎች ግዥ |
20,000 |
|
ሎት 5 |
የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ |
30,000 |
|
ሎት 6 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ |
15,000 |
|
ሎት 7 |
የላብራቶሪ ህክምና መሳሪያዎች ጥገና |
10,000 |
|
ሎት 8 |
የተለያዩ ህትመቶች እና የሰራተኛ መታወቂያና ባጅ |
15,000 |
|
ሎት 9 |
የካልብሬሽን ሰርቪስ አገልግሎት |
10,000 |
|
ሎት 10 |
የጤና ጣቢያው አጠቃላይ የህንፃ እድሳት ስራ |
30,000 |
|
ሎት 11 |
የጀነሬተር እና የላውንደሪ ማሽን ጥገና |
15,000 |
|
ሎት 12 |
የCPD አሰልጣኝ ባለሙያ |
10,000 |
|
ሎት 13 |
የኮምፒውተር፣ የላፕቶፕ፣ የፎቶኮፒ፣ የፕሪንተር ጥገና |
10,000 |
|
ሎት 14 |
የሰራተኛ ካፍቴሪያ አገልግሎት እና የምግብና የመጠጥ አቅርቦት |
30,000 |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የታክስ ግዴታውን የሚያመላክቱ ሰነዶች፣ የአቅራቢነት ምዘገባና የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ እና አነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት ለሚወዳደሩበት ዘርፍ የድጋፍ ደብዳቤ ማስረጃ በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደሩበትን እቃ ዋጋ እስከነ ቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል።
እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በትክክል በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ወይም ኢንቬሎፕ በማድረግ የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶኮፒውን በተናጥል አሽገው የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በመሿለኪያ ጤና ጣቢያ የግዥ ክፍል በር ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የጨረታው ማስከበሪያ አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈፀም ድረስ እንደተያያዘ ይቆያል።
ተጫረቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ከ7 ቀን በኋላ 10% የውል ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ እሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል። መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን እቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ቢሮ ቁጥር 38 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
በ11ኛው ቀን በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
የጨረታው ሰነድ በመሿለኪያ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 07 ረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው እስፔስፍኬሽን መሰረት ሲሆን ለሁሉም እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ደብረዘይት መንገድ ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ማሳሰቢያ- ይህ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ወይም ከክፍል 1 እና 7 ውጭ ያሉት ገጾች ኮፒ በማድረግ የሚጠይቀውን መጠይቅ በመሙላት እያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም፤ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ መመለስ አለበት፣ ማሳሰቢያው ተግባራዊ ካልሆነ የሚቀርበው ጐደሎ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ግዥ ክፍል በስልክ ቁጥር 011 470 0810 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-24 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kirkos Sub City Meshualekiya Health Office
- Buyer address: ደብረዘይት መንገድ ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T09:00:00.000Z
- Source: 2merkato