Textile, Garments and Uniforms
በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና የጥገና ግብዓቶችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር/ግ/ጨ 001/ 2019 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና የጥገና ግብዓቶችን፡- በአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ፤
- በኣቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ በዌብሣይት የሚረጋገጥ፤
- እንደአስፈላጊነቱ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ለህክምና ዕቃዎች ግድ ነው * ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 በሚገኘው የግዢ ክፍል ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጤና ጣቢያው ስም በተከፈተው መደበኛ የሂሣብ ቁጥር 1000056592141 ገቢ በማድረግ ባንኩ የሚሰጠውን ደረሰኝ በማያዝ ወይም በጥቃቅንን እና አነስተኛ ለተደራጁ ከአደራጃቸው ወረዳ የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ በማምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደርበት ዕቃዎች ናሙና በዕቃው ዓይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች ከተቋሙ በወሰዱት ሰነድ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዋና እና ኮፒ ሠነዶችን እንዲሁም ለናሙና የሚቀርቡ የዕቃውን ስም የሚገልፁ የዕቃዎች ናሙና እና የፎቶግራፎች ናሙና ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ለተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚደረግ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን: -
|
የሎት ቁጥር |
የሎት መግለጫ |
የጨረታ ማስከበሪያ % |
የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ ግብዓቶች /6211/ |
0.5 |
9,000.00 |
|
ሎት2 |
የደንብ ልብስ የስፌት አገልግሎት/6211/ |
0.5 |
1,000.00 |
|
ሎት3 |
አላቂ የፅህፈት/6212/ |
0.5 |
8,500.00 |
|
ሎት4 |
የህትመት ውጤቶች/6213/ |
0.5 |
5,000.00 |
|
ሎት5 |
ቋሚ እና አላቂ የህክምና ዕቃዎች/6214/ |
0.5 |
20,000.00 |
|
ሎት6 |
ያለፈባቸው መድሀኒቶች የማስወገድ አገልግሎት/6214/ |
0.5 |
1.5000.00 |
|
ሎት7 |
የካፌ አገልግሎት የሚሰጥ |
0.5 |
14,000.00 |
|
ሎት8 |
የፅዳት ዕቃዎች/6218/ |
0.5 |
7,500.00 |
|
ሎት9 |
ልዩ ልዩ ዕቃዎችና መሣሪያዎች/6219/ |
0.5 |
5,000.00 |
|
ሎት10 |
ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎቶች/6243/ |
0.5 |
1,500.00
|
|
ሎት11 |
ልዩ የጥገና ዕቃዎች/6243 እና 6244 |
0.5 |
3,000.00 |
|
ሎት12 |
ልዩ ልዩ የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎቶች የውሀ መስመር፤ የመብራት መስመር፤ የፍሣሽ መስመር እና ጄኔሬተር /6244/ |
0.5 |
2,000.00
|
|
ሎት13 |
ኤሌክትሮኒከስ የሆኑ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች/6313/ |
0.5 |
15,000.00
|
|
ሎት14 |
ፈርኒቸር የሆኑ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች/6313/ |
0.5 |
5,000.00 |
|
ሎት15 |
ልዩ ልዩ አገልግሎቶች |
0.5 |
2,000.00 |
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በዘረፉ ከተደራጁበት ወረዳ ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ አስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሠነድ መቀበያ ጊዜ የበቃ መሆኑን የሚገልፅ ቃለጉባኤ በመያዝ ተዘግቶ በዚያው ዕለት እና ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ 3፡30 የመክፈቻ ቃለጉባኤ ተይዞ ሲታሸግ የነበሩ ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል። በዚህ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲገኙ ይጋበዛሉ፤ባይገኙ ግን የጨረታ መዝጊያውንም ሆነ መከፈቻ ቀኑን ወይም ሰዓቱን ማራዘም አይቻልም፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር: 0112-29-12-50 ወይም በኢሜይል አድራሻችን፡- [email protected] ወይም ሊያገኙን ይችላሉ፡፡ አድራሻ፡- ከአውቶብስ ተራ ወደ ሰባተኛ ወይም ከሰባተኛ ወደ አውቶብስ ተራ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ሲሄዱ ከዋይ ዜድ ህንፃ ወደ መካነ ሠላም ሆቴል በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ያህል እንደሄዱ ባለ አራት ፎቅ ህንፃ ላይ /በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ በሚል ስያሜ ያገኙናል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ አስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00
- Bid opening: 2026-09-24 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ አስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ketema Sub City Health Office Woreda 8 Millennium Health Center
- Buyer address: ከአውቶብስ ተራ ወደ ሰባተኛ ወይም ከሰባተኛ ወደ አውቶብስ ተራ በሚወስደው አስፓልት መንገድ ሲሄዱ ከዋይ ዜድ ህንፃ ወደ መካነ ሠላም ሆቴል በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ያህል እንደሄዱ ባለ አራት ፎቅ ህንፃ ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ በሚል ስያሜ ያገኙናል
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T09:20:39.000Z
- Source: 2merkato