Finishig Works

ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አክሲዮን ማህበር በሕንጻ ውስጥ ያለውን የፓርኪንግ ቦታ መሬቱን ልሾ እና በቀለም ለማስዋብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አክሲዮን ማህበር በሕንጻ ውስጥ ያለውን የፓርኪንግ ቦታ መሬቱን ልሾ እና በቀለም ለማስዋብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት

  1.  በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችል
  4.  የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር )ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 ( አንድ ሺ ብር ) በመክፈል ዘወትር ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ  ቀኑ 10፡30 ድረስ አከሲዮን ማህበሩ ገንዘብ ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱንና የተጫራቾች መመሪያ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /በታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  10.  አሸናፊው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የስራ ውል መዋዋል አለበት፡፡

አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስ.ቁ 011 2 79 30 65

ታህሰብ የንግድ ስራዎች አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር )ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡30
  • Bid opening: 2026-09-22 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tahseb Business S.C.
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T09:23:49.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders