Spare Parts and Car Decoration Materials

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ የህትመት አግልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2019

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሎት አንድ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ ሎት ሁለት የህትመት አግልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም

.

የዕቃው ዓይነት

ኪያ

ምርመራ

1

ሎት አንድ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ

በቁጥር

የሎት 1 እና የሎት 2 ዕቃዎች ብዛት እና ዓይነት ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል

2

ሎት ሁሉት ዓመታዊ የህትመት አገልግሎት ግዥ

በቁጥር

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ እና ሌሎች ያሏቸውን ማስረጃዎቻቸውን በግልፅ ሊነበብ በሚችል መልኩ አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው።

  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ሎግታ አጠገብ ሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ፣ ቢሮ ቁጥር 18 ሀዋሳ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 10,000.00 አስር ሺህ ብር በባንክ የተመሰከረለት CPO ብቻ ለእያንዳንዳቸው ሎት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ፕሮፎርማ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒና ኦርጅናል በአንድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ጨረታው ከታወጀበት እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 ሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሎጊታ አጠገብ ሀዋሳ ይከፈታል።
  • መ/ቤቱ ከጠቅላላው የግዥ መጠን (ብዛት) ላይ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ነገር ግን የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት እና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ባይሆን የጨረታዉ ሳጥን የማሸጉም ሆነ የመክፈት ሥነሥርአት የምከናወነው በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0916 025 922 ወይም 0912 462 506 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-23 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama Regional State Culture, Tourism and Sport Bureau
  • Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T09:56:16.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders