Vehicle and Machinery Sale
አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሉ 2 (ሁለት) ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ቁጥር ጨ002/18
የጨረታ ማስታወቂያ
አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሉ 2 (ሁለት) ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ተሽከርካሪዎቹን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከኘሮፐርቲና ፋሲሊቲ መምሪያ መውሰድ ይችላሉ።
2. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ቅጥር ግቢ ኘሮፐርቲና ፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ ፊት ለፊት በመገኘት መመልከት ይቻላል።
3. ተጫራቾች የተሸከርካሪዎቹን ይዞታ በማየት የሚሰጡትን ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ መጻፍ ይኖርባቸዋል። ሆኖም በፊደልና በቁጥር የተጻፈው ዋጋ ልዩነት የሚኖረው ከሆነ መ/ቤቱ ትልቁን ዋጋ በመያዝ ጨረታውን ያወዳድራል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ሞልተው የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (15%) ጨምሮ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከ03/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ቅጥር ግቢ ኘሮፐርቲና ፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ በመሄድ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
5. ጨረታው መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ቢሮ ፊት ለፊት ይከፈታል።
6. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት የለውም።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 20% (ሃያ መቶኛ) CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። CPO ከጨረታ ሠነድ ጋር በፖስታ ታሽጐ መቅረብ አለበት። ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል።
8. የጨረታ አሸናፊው ከጨረታው በኃላ ያሉትን የስም ማዘዋወሪያ ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።
9. አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በሶስት (3) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረታቸውን አለባቸው። ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት " የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባያው ገቢ ይደረጋል።
10. ማንኛውም የመንግስት ዕዳ ቢኖር ሻጭ ይከፍላል።
11. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-24 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Alsam PLC
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Sep 13, 2026)
- Posted at: 2026-09-14T12:05:55.000Z
- Source: 2merkato