Stationery
የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኝ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesSpare Parts and Car Decoration Materials
Amhara
More tags
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesFuel and LubricantsInstallation, Maintenance and Other Engineering ServicesOffice Machines and ComputersMaintenance and RepairAmharic2merkatoMetema Wereda Finance and Economic Development Bureau
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኝ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት
- ሎት 1. ልዩ ልዩ የጽ/መሳሪያ፣
- ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች (ስፔር ፓርት)፣
- ሎት 3. የመኪና ጎማ፣
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 5. መኪና ዘይት እና ቅባት፣
- ሎት 6 የኮምፒውተር ወረቀት፣
- ሎት 7. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና የእጅ ዋጋ እና
- ሎት 8. ልዩ ልዩ የኮምፒወተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡። ገዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ሎት 1. ልዩ ልዩ የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች (ስፔር ፓርት)፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ፣ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5. መኪና ዘይት እና ቅባት፣ ሎት 6. የኮምፒውተር ወረቀት ሎት 7. ኤሌክትሮኒከስ ጥገና የእጅ ዋጋ፣ ሎት 8. ልዩ ልዩ የኮምፒወተር የቀለም ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታጠቁ ባንኮች (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በመሂ1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ዋጋ 1 በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ገዥውን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ በማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስከበሪያ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 30 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ 16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ዓመታዊ ውል ስለሚሆን የጨረታውን ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ 20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናውን እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ታሽጎ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በየሎቱ በጥቅል ሰለሆነ የሙሉ ዕቃ ዋጋ መሞላት አለበት ካልተሟላ ግን ከጨረታው ውጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና ዕቃዎችን መተማ ወረዳ ንብረት ክፍል በዝርዝር ማሰረከብ የሚችል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 00 47 በመደውል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሽናፊው ዕቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ስርዝ /ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሽናፊው ድርጅት የውል ማሰከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ሲፒኦ በማስያዝ በወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል መውሰድ የሚችል፡፡
- ልዩ ልዩ የጽ/መሳሪያ ጨረታ በተመለከተ ዕቃዉ ወደ ንብረት ክፍል በዝርዝር ገቢ ከመደረጉ በፊት ኦርጅናል መሆን አለመሆኑን በሚመለከተዉ ባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ ወደ ንብረት ክፍል ዕቃዉ ገቢ ማድረግ የሚቻለዉ፡፡
- ጊዜያዊ የሚል ንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ሰርተፊኬት ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
- Bid opening: 2026-09-29 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Metema Wereda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Be'kur (Sep 14, 2026)
- Posted at: 2026-09-14T12:39:21.000Z
- Source: 2merkato