Transportation Service
ኢትዮ ሬይል ሎጅስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባለ 20 እና ባለ 40 ጫማ ኮንቴነሮችን፤ የብትን ጭነቶች (Break-bulk Cargo) ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ (Export) እና ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ (import) ለማጓጓዝ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: ERL PD/ NCB/3/2019 EC
ኢትዮ ሬይል ሎጅስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባለ 20 እና ባለ 40 ጫማ ኮንቴነሮችን፤ የብትን ጭነቶች (Break-bulk Cargo) ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ (Export) እና ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ (import) ለማጓጓዝ ይፈልጋል:: በመሆኑም ብቃቱ ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በሚከተለው መረጃ መሰረት ይጋብዛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመስከረም 7/ 2019 -መስከረም 20/2019 ዓ.ም በተገለጸው አድራሻ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ከሰአት 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው:
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 20 ቀን 2019 ከሰአት 8፡30 በኢትዮ-ሬይል ሎጂስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው ቋንቋ እንግሊዘኛ ወይም አማርኛ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የቲን መመዝገቢያ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ከጨረታው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች የንግድ የምስክር ወረቀት ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ኢትዮ- ሬይል ሎጂስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ እና ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ኢትዮ-ሬይል ሎጂስቲክስ ኃ.የተ.የግ.ማ የግዥ አስተዳደር ቡድን መሪ
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሿለኪያ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር ግቢ
ስልክ +251114397665/+251114377023
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-30 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮ ሬይል ሎጅስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 16, 2026)
- Posted at: 2026-09-16T11:21:52.000Z
- Source: 2merkato