House, Building and Warehouse
ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕብር ሕንፃ ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለልን ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሕባ/001/2019
ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕብር ሕንፃ ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለልን ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል:: ስለሆነም ኪራይ ፈላጊዎች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነድ ሊያቀርቡ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣ ከ2 ቀናት በኋላ ማለትም ከመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በአቅራቢያ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር IN0403007 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ወለል በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በመገኘት መግዛት ይቻላል።
- ለጨረታ የቀረበውን ወለል / ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ማለትም ከመስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. ውስጥ ሰኞ፤ ዕሮብ እና አርብ ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡00 ሰዓት በባንኩ ዋና መ/ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለጨረታ የቀረበውን ይዞታ ቢከራዩ የሚከፍሉትን የአንድ ወር ኪራይ አንድ አራተኛ (25%) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርቡ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የዋስትናው የአገልግሎት ጊዜውም Walidity Date/ ዘጠና (90) ቀናት ይሆናል፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስይዙትን የባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የሚያሰሩት ከሕብረት ባንክ ውጪ በሆኑ በማንኛውም ባንኮች መሆን አለበት።
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በማሟላት ልደታ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 7፣ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በሚገኝ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ መስከረም 19፣ 20 እና 21 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አራተኛ /4ኛ/ ወለል ላይ በሚገኘው አዳራሽ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ/ተጫራች ከውድድር ሊሰረዝ ይችላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 470 41 72 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!!
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): መስከረም 19፣ 20 እና 21 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 10:00
- Bid opening (note): መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hibret Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 16, 2026)
- Posted at: 2026-09-16T13:04:07.000Z
- Source: 2merkato