Spare Parts and Car Decoration Materials

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የSupply 12V150A Battery ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/ SB/121/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ግአገልግሎት የሚውል የSupply 12V150A Battery ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የዕቃው አይነት

የፕሮጀክት

ስም

የጨረታ ቁጥር

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

Supply 12V150A Battery

ዋና /ቤት

 

DCE/SB/121/2026

 

መስከረም 22/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00

መስከረም 22/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30

50,000.00

 

ስለሆነም፦

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅረቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘዘገቡ መሆኑን ሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክየተሰጠና የተረጋገጠ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞው መ.ኮ.ድ ግቢ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

E-mail አድራሻ [email protected]  የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com  

ፖ.ሳ.ቁ 3414

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-02 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 17, 2026)
  • Posted at: 2026-09-17T08:08:05.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders