Personal Care Products and Services

በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር03/2019

በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ

  • የተለያዩ ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች፣
  • አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣
  • የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች፣
  • ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣
  • ስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች እና
  • ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች

 በሀራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2019 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. በጨረታው ሸያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን፤ በሀራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
  3. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለምድብ 1 ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)፤ ለምድብ 2 አልባሳት ዘርፍ እቃዎች ብር 51,000 (ሃምሳ አንድ ሺህብር)፣ ለምድብ 3 አልባሳት ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህብር)፣ ለምድብ 4 ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ ለምድብ 5 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህብር) ለምድብ 6 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ ለምድብ 7 ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)፤ ለምድብ 10 ስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ለምድብ 11 ልዩልዩ  ዘርፍ እቃዎች ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 13/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ መገኘት አለባቸው።
  4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9፡00-12፡00 የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 13/01/2019 ጠዋት 3፡30 ሰአትድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።
  6. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 13/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00- 6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9፡00- 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ሳያዩ በሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም።

7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ። 

.

//ቤቱ ስም

 

የጨረታው አይነት

 

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ጋላፊ ጉምሩክ //ቤት

ሀራጅ ጨረታ

እስከ 13/01/2019 ከጠዋቱ 330 ድረስ

13/01/2019 . ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

 

8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጅናል ይዘው መቅረብ አለባቸው።

9. በተጫራቾች የተሰጠ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

10. በጨረታ ለሚሸጥ እቃ የጨረታ ውጤት እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል።

11. ምድብ ለወጣላቸው ሀራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል። በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው።

12. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል።

13. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

14. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ የመረከብ ግዴታ አለበት። በተጨማሪም ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።

15. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

16. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።

17. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች የሚገኙበት ቦታ ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ።

18. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት

ስልክ ቁጥር 033-559 0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-23 10:00
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:10:01.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders