Spare Parts and Car Decoration Materials
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የገዥው መለያ ቁጥር: ት/ልአ/ዘ ግዥ ብ/ግ/ጨ/01/2016
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ከዚህ በታች ለተጠቀሱት የተለያዩ መለዋወጫዎች፡-
- (lveco, Tracker, lsuzu, Nisan and Eitcher Toyota,
- Hyundai Dongfong, Daewoo bus, Sunlong bus,
- ZNA rich pickup,
- Kia Automobile,
- Lifan Automobile and Addis Geely Automobile የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ
በማወዳደር የግዥ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል በመዋዋል (በማዕቀፍ ስምምነት) ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት
በጨረታው ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፋ ለ2018/2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከ ሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እነዚህ ሰነዶች በኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በማሸግና በመግለጽ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከመስከረም 11/2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት ድረስ ግዥ ክፍል አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው የመኪና ዕቃ መለዋወጫ፡- ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲው ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ በማሸግና ኮፒ እና ኦሪጅናል የፋይናንሻል እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች በማድረግ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። አድራሻ ከታች ተገልጿል።
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን 10 ፐርሰንት /አስር ፐርሰንት/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ እቃው በመነጋጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል በመዋዋል በውሉ መሰረት የምንረካከብ ይሆናል።
- ዘርፉ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
የሀብት አስተዳደርና ግዥ ዋና ክፍል
አድራሻ፡ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጣሳና ኮርኪ ፋብሪካ ፊት
ለፊት ሸገር ህንፃ
አከባቢ አለ በጅምላ ጊቢ ውስጥ
ስልክ ቁጥር፡- 011 4552358
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-10-02 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
- Posted at: 2026-09-18T09:21:17.000Z
- Source: 2merkato