Spare Parts and Car Decoration Materials

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/03/2019(NCB)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማ ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መወዳደር ይችላሉ።

የዕቃው ዓይነት

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ

1

200,000.00

መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት

መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት

 

 

2

250,000.00

 

3

170,000.00

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ፤

2. የጨረታ ሰነዱን መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ.ኤ.አ ፕሮጀክቶች ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በአ.ኤ.አ. አአአአፕ ወይም EEU-UEAP ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/03/2019 (NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እና የሎት ቁጥሩን በመፃፍ ከላይ በተራ ቁጥር-2 በተገለጸው አድራሻ እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ መስከረም 26 ቀን 2019 ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል።

6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00_6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ።

7. የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111263159 መደወል ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-06 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:32:12.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders