Spare Parts and Car Decoration Materials

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ ተሽከርካሪ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቀላል መኪና ጎማዎችና የከባድ መኪና ጎማ እና የደንብ ልብስ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በያዘው እቅድ መሰረት፡-

  • ሎት 1 ለጽ/ቤቱ ተሸከርካሪ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቀላል መኪና ጎማዎችና የከባድ መኪና ጎማ ግዥ፣
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ ግዢ ለመፈጸም በማቀድ የወጣ የግልጽ ጨረታ የተጫራቾች መመሪያ ነው።
  1.  በግልጽ ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የድረጅታችሁን ስም፣ አድራሻችሁን ስልጣን በተሰጠው የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማችሁን እና ህጋዊ ማህተማችሁን በማሳረፍና የዋጋ ማቅረቢያውን ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ ቤት በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ለግልጽ ጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ መመሪያ በደንብ ማንበብ ዋጋ ሲሞላ ከሚደርሰው ስህተት ያድናል።
  3. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስህተት ቢኖረው የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት ስህተቶቹን በጽሑፍ በማረምና በሌላ ፖስታ በማድረግ ፖስታው ላይ የተሻሻለ ወይም የተለወጠ የሚል ጽሑፍ ጽፎ በግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም አቅርቦ ቢገኝ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
  5. የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የሚሰጡት በግልጽ ጨረታው የሚያቀርቡትን የተወዳደሩበትን ዕቃ ዓይነት፣ መለኪያ እና የአንዱን ዋጋ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ መሆን ይገባዋል።
  6. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፣ በእርሳስ እና በቀይ እስክርቢቶ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. ማንኛውም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ያቀረበውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ውድድሩን ትቻለሁ ቢል ለግልጽ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ይቀጣል እንደ አስፈላጊነቱም መ/ቤቱ ወደ ፊት በሚያወጣው ግልጽ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ሊያደርግ ይችላል።
  8. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን የዕቃ አቅርቦት ዋጋ በግልጽ ጨረታ ሰነዶች ላይ ባቀረቡት ዋጋ ብቻ ለመ ቤታችን ማቅረብ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች በዝርዝር በተገለጹት የዕቃ ዓይነቶች ባላቸው የፍቃድ አይነት የዕቃ አይነቶች በሙሉ ሆነ በከፊል መወዳደር ይጠበቅባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታውን ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በግልጽ መረዳትና በተግባር ላይ ማዋል አለባቸው።
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የዕቃ ሽያጭ ዋጋ ሁኔታ መ/ቤቱ በጠየቀው እስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን አለባቸው።
  12. ተጫራቾች ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን የቫት ተመዝጋቢና የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ከዋናው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  13. ግልጽ ጨረታው በአየር ላይ ከሚቆይበት ቀናቶች ውጪ ዘግይተው የሚቀርቡ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  14. ግልጽ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በመጨረሻ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በማስታወቂያ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  15. ግልጽ ጨረታው በተጫራቾች ፊት በግልጽ ይነበባል፣ የግልጽ ጨረታ አከፋፈት ዝርዝር ቃለ ጉባዔ ተይዞ በመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ ይፈረማል እንዲሁም በግልጽ ጨረታው አከፋፈቱ ላይ የተገኙ  ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በግልጽ ጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ስለመገኘታቸው  እንዲፈራረሙ ይደረጋል።
  16. የአገልግሎት ጊዜው መ/ቤት የግልጽ ጨረታውን አሸናፊውን ከለየ በኋላ ለአሸናፊው ድርጅት በጽሁፍ ያሳውቃል።
  17. የአገልግሎት ጊዜው መ/ቤት የግልጽ ጨረታ አሸናፊውን ለይቶ ካሳወቀ በኋላ በ3 ቀናት ውስጥ በቀረበው ዋጋ መሰረት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይገባል።
  18. የግልጽ ጨረታን በሚመለከት ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዳው ለማንኛውም ኃላፊ እና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከግልጽ ጨረታው የሚሰረዝ እና አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ የሚሰረዝ መሆኑንና በህግ የሚያስቀጣው እንደሆነ ማወቅ ይኖርበታል።
  19. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ለእያንዳንዱ ሎት ሲፕኦ (CPO) 20,000 /ሃያ ሺህ/ ማስያዝ ይኖርበታል ቢድ ቦንድ ማስያዝ ፈጽሞ አይፈቀድም።
  20. በዚህ የግልጽ ተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን ያልፈጸመ በተራ ቁጥር 19 ላይ የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ሊያስቀጣው ይችላል።
  21.  ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማያያዝ ግልጽ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቤ/ጉ/ክልል አሶሳ ከተማ በሚገኘው በጽ/ቤቱ ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  22. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ግልጽ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  23. ሁሉም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን በፊት ሙሉ በሙሉ የግልጽ ጨረታ ሰነዳቸውን ቀድመው ካስገቡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜውን ሳይጠብቅ ለተጫራቾች በስልክ ጥሪ ተደርጎ ይከፈታል።
  24. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ አሶሳ ከተማ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል።

አድራሻ ስልክ ቁጥር 09 21-17-78-90 / 057-775-24-99 / 057-775- 0142 / 057-775-00-31 /

09 15-89-09-36

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በመጨረሻ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-02 14:10
  • Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በመጨረሻ ከቀኑ 8፡10 ሰዓት
  • Region: Beneshangul Gumuz
  • Publishing entity: Benishangul Gumuz Regional State Administration Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:33:30.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders