Textile, Garment and Leather

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 ውስጥ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 ውስጥ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ፡

  • ሎት1 የቢሮ የተለያዩ የፅሕፈት መሣሪያ ዕቃዎች፣
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 3 የሕክምና ዕቃ፣
  • ሎት 4: የላብራቶሪ ዕቃ፣
  • ሎት 5 የፅዳት ዕቃ፣
  • ሎት 6 ቋሚ ዕቃ፣
  • ሎት 7 የጥገና ዕቃ፣
  • ሎት8 የኅትመት ሥራ
  • ሎት 9 የውሃ መስመር ጥገና የኤሌክትክ መስመር ጥገና

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ማንኛውም የዘርፉ ሕጋዊ ነጋዴዎች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያገኙበት ቦታ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ በሎት 100 /መቶ ብር ብቻ/ ከፍሎ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3. ለሎት 4፣ ለሎት 5 ለአምስቱም ሎቶች 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ እና ለሎት 6፣ ለሎት 7፣ ሎት 8 እና ሎት 9 ለአራቱም ሎቶች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን ቀደም ብሎ የድርጅቱን ሙሉ ስምና ሕጋዊ ማኅተም በማድረግ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ገዢው አካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

6. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ለመዋዋል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።

7. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው እቃዎች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ቆይቶ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀን እስከ 11፡30 ስዓት ቆይቶ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጐ በ11ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. የእቃ ማጓጓዣ አሸናፊው ድርጅት ይሸፍናል።

10. ተጫራቾቹ የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካለ ውድቅ ይሆናል።

11. ተጫራቾቹ የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት። የአንዱን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ካልተሞላ ውድቅ ይሆናል።

12. ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅ ተቋም በኃላፊው የተፃፈ ወቅታዊ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው። በባለሙያ የተፃፈ ከሆነ ተቀባይነት የለውም።

13. ይህ ጨረታ 11ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ወደ ቀጣይ የሥራ ቀናት ይሻገራል።

14. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: ካራ ቆሬ ወደ ወለቴ መሄጃ ረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አለፍ ብሎ በተለምዶ ጥላሁን ሜዳ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 3

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 835-3416 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 ረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀን ቆይቶ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-30 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀን ቆይቶ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Repi Japan Primary School
  • Buyer address: ካራ ቆሬ ወደ ወለቴ መሄጃ ረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አለፍ ብሎ በተለምዶ ጥላሁን ሜዳ የረጲ ጃፓን የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 4
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር በሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:46:50.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders