Vehicle and Machinery Sale

አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ሁለት የጣልያን አይቪኮ እንዲሁም በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ የ2017 ሞዴል ሊፋን X60 ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ የም/አም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ሽያጭ /0006/2026

አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ሁለት የጣልያን አይቪኮ (Model 50C15/E3 Year: 2020፣ Chassis no.: EBPBCAHAALD000015 እና EBPBCAHAALD000016፤ Motor no.: FICE3481J3827324 እና FICE3481J3827326፤ Clour: White፣ Vehicle type: Bus፣ CC: 2998 እንዲሁም በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ የ2017 ሞዴል ሊፋን X60 ቻንሲ ቁጥር LCN64ED50M0097133 ፤ የሞተር ቁጥር LFB479Q*170300359* ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት በጨረታዉ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያመሟሉ ማንኛዉም ተጫራቾች ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መጫረት ይችላሉ።

1. ማንኛዉም የመጫረት ፍላጎት ያለዉ በጨረታዉ ላይ መሳተፍ ይችላል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሸከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋዉን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ዉጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለዉም።

3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሽከርካሪው አዳማ በሚገኘዉ የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊዉ ተለይቶ ከታወቀ በኃላ የሚመለስ ይሆናል።

5. የጨረታዉ አሸናፊ ለተሽከርካሪዉ የሚከፈሉ ማንኛዉንም የመንግስት ክፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል።

6. ማንኛውም ተጫራትች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

7. የጨረታዉ አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል። የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀመ ለጫረታ መስከበሪያ የተየዘው ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘዉን ገንዘብ  አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምርያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

9. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዳማ ከተማ በሚገኘዉ የድርጅቱ  ፋብሪካ ቅጥር ግቢ  ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰዉ ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ። በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለዉም።

11. የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየዉ ባቀረበዉ የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነዉ።

12. የጨረታዉ አሸናፊ ጨረታዉን ማሸነፉ በተገለጸ  በ7 ቀናት ዉስጥ በአካል ቀርቦ ዉል መፈፀም አለበት።

13. የጨረታዉ አሸናፊ ዉል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ 7 ቀናት ዉስጥ ቀርቦ ዉል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘዉን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል።

14. ድርጅቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፤- 09 84 55 11 86/ 09 73 30 00 59


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-06 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: 2merkato.com (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T07:09:04.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders