Steel Raw Materials and Products
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን በስሩ ለሚገኙ 14 ደንበኞች አገልግሎት ማዕከላት የመዝገብ ቤት እና የዕቃ ግ/ቤት ሼልፍ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ሽ/ሪ/ግ/ጨ/002/2019
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን በስር ለሚገኙ 14 ደንበኞች አገልግሎት ማዕከላት የመዝገብ ቤት የዕቃ ግ/ቤት ሼልፍ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
የዕቃው አይነት |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
|
የመዝገብ ቤት እና የዕቃ ግ/ቤት ሼልፍ |
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት |
ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ከገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ https://epg.ppa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር በላይ 400 (አራት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000482105592 EEU-ፊንፊኔ ዙሪያ ዲስትሪክት በሚለው በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- አድራሻ፡- 22 ድንበሯ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) “Ethiopian Electric Utility-Sheger Region” ስም የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል።
- የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ኢ/ኤ/አ/ሸገ/ሪጅ/ግ/ጨ/002/2019 የሚል በማድረግ እስከ መስከረም 22/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን በዚያው ቀን መስከረም 22/2019 ዓ.ም 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘብት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-011-522-65-04 መደወል ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-02 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T08:49:26.000Z
- Source: Qelal Tenders