Textile, Garments and Uniforms
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ የተለያዩ አይነት ያላቸውን እቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ድፍጤጣ/ግልጽ/ጨ/01/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን እቃዎች እና አገልግሎቶችን ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
- ሎት1.ጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳ ጫማ ውጤቶችና ተዛማጅ (የደንብ ልብስ)
- ሎት2. የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት3. የህትመትና ተያያዥ ስራዎች
- ሎት4. መድኃኒት እና የህክመና ማሽን ሪኤጀንቶች
- ሎት5. የቢሮ ፅዳት መገልገያ እቃዎች
- ሎት6. የቢሮ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች
- ሎት7. የቢሮ ቋሚ የእንጨት ውጤቶች
- ሎት8. የመኪና ጎማና ቅባቶች
- ሎት9. የሰራተኞች ልብስ ስፌት አገልግሎት
- ሎት10. የአትክልትና የግቢ ማስዋብ ግብዓቶች አገልግሎት
- ሎት.11 የቢሮ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና
- ሎት12. የሮቶ ውኃ ምርመራ
- ሎት13. የኦክስጅን መሙላት አገልግሎት
- ሎት14. የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና እና የህንጻ ጥገና
- ሎት15. የመስተንግዶ ግብዓት ግዥ ማቅረብ
- ሎት16. የመጫንና የማውረድ አገልግሎት (ጉልበት ሰራተኛ)
- ሎት17. የጭነት መኪና እና አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና አገልግሎት
በዚህም መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን የቴክኒክ መመዘኛ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
1.ከሎት አንድ እስከ ሎት 16 ያሉት በዘርፉ የተሰማሩ የ2018/2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት (egp)፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የታደሰ ግብር ከፋይነት ከሊራንስ የምስክር ወረቀት ያለው ማቅረብ የሚችል።
2. በሎት 4,16,እና 17 ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አይጠበቅባቸውም
3. በሎት 15 እና16,17 ለአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የማይገደዱ ሲሆን በሎት 16 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ ማቅረብ ያለባቸሁ ሲሆን፣ ሎት 17 ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ፣ሊብሬ ኮፒ፣ መኪናው ለመድኃኒት ጭነት አመች የሆነ ሽፍን እንዲሁም መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሲሆን ነዳጅና ሌላ የመኪና ፍጆታዎች በራሱ መሸፈን የሚችል፤
4. በሎት 14 ላይ የምትወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ከደረጃ 7ና በላይ መሆን ያለባችሁ ሆኖ የጨረታ ሰነዳቸው ቴክኒካል መረጃዎች ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
5. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱ ሎት ክፍያ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 901 በመፈጸም የጨረታ ሰነድ ከግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 907 መውሰድ አለባችሁ። አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።
6. ጨረታው ለ10 (አስር ቀን) የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም የጨረታውን መክፈቻ የሚያስተጓጉል አይሆንም።
7. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋጋጠ CPO ለሎት1 ብር 13,000.00፣ ሎት2 ብር 22,000.00፣ ሎት3 ብር 24,000.00፣ ሎት4 ብር 10,000.00፣ ሎት5 ብር 24,302.00፣ ሎት 6.ብር 20,000.00 ሎት7 ብር 20,000.00 ሎት 8.ብር 15,000,ለሎት 9.ብር 10,000.00,ሎት 10.ብር 5,000.00፣ ለሎት 11.ብር 5000.00፣ ለሎት 12 ብር 5,000.00, ሎት 13.ብር 5,000.00 ሎት 14 ብር 34032 ሎት 15.ብር 5,000.00.ሎት 16.ብር 1,000.00 እና ሎት 17 ብር 1000.00 በድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ስም በማሰራት ከሚያቀርቡት ቴክኒካል መረጃ ጋር አሲዘው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስም ፣ ማህተም፣ ፊርማ በማድረግ የጨረታውን አይነት ሎት በግልጽ በመግለጽ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
9. ተጫራቾች የእቃ ናሙና እና በፎቶ ለተጠየቁባቸው እቃዎች ወይም አገልግሎት ናሙናውን ቀድመው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በዝርዝር አስመዝግበው ማቅረብ አለባቸው። የደንብ ልብስ ስፌት የ2018 ዓ.ም መልካም አፈጻጸም ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅበታ።
10. ጤና ጣቢያው በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በጨረታ በግዥ ትዛዝ ላይ 20% የመጨመር እና 20% የመቀነስ መብት አለው። እንዲሁም አሸናፊው ማሸነፉን ከተገለጸለት በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ከጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ በድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ስም አሰርቶ ማስያዝ አለባቸው።
11. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ጤ ጣቢያው አድራሻ መጋዘን አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
13. ጤ/ጣቢያው ለሚፈጽመው ግዥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251-98 805 3333
አድራሻ፡-ገርጂ መብራት ሀይል ሰብስቴሽን ጀርባ በቪሽን ት/ቤት ኮብል ስቶን መንገድ ገባ ብሎ
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-10-02 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dil Fire Health Post
- Buyer address: ገርጂ መብራት ሀይል ሰብስቴሽን ጀርባ በሚሽን ት/ቤት ኮብልስቶን መንገድ ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T09:10:57.000Z
- Source: Qelal Tenders