Steel Raw Materials and Products

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለውሃ ቁፋሮ ስራ አገልግሎት የሚውል የዕቃ አቅርቦት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB WWC 01/2019

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) ለውሃ ቁፋሮ ስራ አገልግሎት የሚውል የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 01/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተ.ቁ

 

የሎት ቁጥር

ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር ዓይነት Summery of goods

መለኪያ

ብዛት

ምርመራ

 

1

ሎት-1

 

Difference types of Steel Casing

በቁጥር

 

625

 

 

2

ሎት-2

 

PH/EC/TDS/Temperature portable meters (Por table water Quality kit)

Set

 

5

 

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/፤የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለሎት 1 ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/፣ለሎት-2 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡

3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 /ሃያ/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ክፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል/ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክትሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡

6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቀጥር- 058-222-14-79 መጠየቅ ይቻላሉ፡፡

8. ማሳሰቢያ፤- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጂ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

አድራሻ: - ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 የድሮው አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ፖ.ሣ.ቁ 106, ስልክ ቁጥር 058 222 1479

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-09 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Water Works Construction Enterprise
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T09:22:19.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders