Equipment and Accessories
ዳሽን ባንክ አማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለአንደኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ለመሸጥ የተዘጋጀ ሽያጭ DB/050/2019
ዳሽን ባንክ አማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለአንደኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1.ተጫራቾች ቄራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በባንኩ መጋዘኖችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።
5. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
6. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከዳሽን ባንክ አማ. ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በ10ኛው ቀን ማለትም መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ06፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ09፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
8. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠርከ 3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውልማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ውል በፈረሙ በ10 የሥራ ቀናት ዉስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውልማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-465 5552፣ 011-470 6065 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
12. ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ዳሽን ባንክ አ.ማ.
አዲስ አበባ
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ADDING MACHINE |
በቁጥር |
3 |
|
2 |
ELECTRICAL TYPEWRITER |
በቁጥር |
1 |
|
3 |
QUEUING MANAGEMENT SYSTEM |
በቁጥር |
2 |
|
4 |
SWICH |
በቁጥር |
26 |
|
5 |
Monitor/System unit |
በቁጥር |
71 |
|
6 |
METAL DETECTOR |
በቁጥር |
60 |
|
7 |
Kama Small Generator |
በቁጥር |
4 |
|
8 |
PHOTO COPY MACHINE |
በቁጥር |
11 |
|
9 |
LOST AND FOUND DISPLAY BOARD |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
10 |
NOTICE BOARD |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
11 |
WALL CLOCK |
በቁጥር |
4 |
|
12 |
EPSON TERMAL PRINTER |
በቁጥር |
35 |
|
13 |
TALLY PRINTER |
በቁጥር |
12 |
|
14 |
UPS/ INVERTER |
በቁጥር |
3 |
|
15 |
FAX MACHINE |
በቁጥር |
9 |
|
16 |
NOTE COUNTING MACHINE FOR CASHER |
በቁጥር |
15 |
|
17 |
NOTE COUNTING MACHINE FOR TELLER |
በቁጥር |
17 |
|
18 |
MANAGERIAL TABLE |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
19 |
SINGLE PEDISTAL TABLE |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
20 |
COMPUTER STAND TABLE |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
21 |
HIGH BACK SWIVEL CHAIR |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
22 |
GUEST CHAIR 3 SEATER |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
23 |
STORAGE CABINET |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
24 |
FILLING CABINET |
በጥቅል |
23 |
|
25 |
LOW BACK SWIVEL CHAIR |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
26 |
GUEST CHAIR |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
27 |
COUNTER CHAIR |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
28 |
SOUND PLAYER |
በቁጥር |
3 |
|
29 |
VIDEO CAMERA |
በቁጥር |
1 |
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-10-01 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dashen Bank S.C.
- Bid bond: 20% ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Fortune (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T11:55:14.000Z
- Source: 2merkato